Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ጥሪ ለወጣቶች

    እግዚአብሔር ወጣቶችን ትጉህ አእምሮ ያላቸው፣ በከበረው ስራው ለተግባር የተዘጋጁና ሃላፊነትን ለመሸከም ገጣሚዎች እንዲሆኑ ይፈልጋል:: እግዚአብሄር ያልረከሰ ልብ ያላቸውን፣ ብርቱና ደፋር የሆኑ፣ ከፊታቸው ያለውን ጦርነት እንደ ጀግና ወንድ ለመዋጋት የወሰኑ፤ በዚህ ድርጊታቸውም እግዚአብሔን የሚያከብሩና ሰብዓዊ ዘርን የሚባርኩ ወንዶችን ይፈልጋል:: ወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስን ቢያጠኑ፣ ችኩል ፍላጎታቸውን መቆጣጠር ቢችሉና የፈጣሪያቸውንና የአዳኛቸውን ድምፅ ማድመጥ ቢችሉ ኖሮ ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም መፍጠር ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ከብረውና ከፍ ከፍ ብለው ያገኙት ነበር:: ወጣት ወዳጄ ሆይ! ሊገመት ከሚችል በላይ ጠቀሜታ ላለው የእግዚአብሔር ቃል መመሪያ ራስህን መስጠት ላንተው ለዘላለማዊ ሕይወት ጥቅም ነው::MYPAmh 22.1

    ብልህ እንድትሆን፣ ከእግዚአብሄር መንፈስ ቁጥጥር ውጭ የሆነና ያልተገራ ህይወትን መምራት ምን እንደሚሆን እንድታስብ አደፋፍርሃለሁ:: «አትሳቱ፣ እግዚአብሄር አይዘበትበትም:: ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል:: ስጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ ከሥጋው ጥፋትን ያጭዳል:: መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ህይወት ያጭዳል::» ለነፍስህ ብለህ፣ ህይወትህን ከጥፋት ለማዳን ራሱን ለሰጠ ለየሱስ ብለህ በህይወትህ ጅምር ላይ ቆመህ ሃላፊነቶችን፣ የተሰጡህን እድሎች፣ ልታደርጋቸው የምትችላቸውን ነገሮች በደንብ መዝን:: እግዚአብሔር ከፍ ያለ መዳረሻን እንድትሞላ እድል ሰጥቶሃል:: የምታሳድረው ተጽዕኖ ለእግዚአብሔር እውነት ሊናገር ይችል ይሆናል:: በሰብዓዊ ዘር ደህንነት ትልቅ ሥራ ውስጥ ከእግዚአብሔር ጋር አብረህ ሠራተኛ ልትሆን ትችላለህ::MYPAmh 22.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents