Go to full page →

ተስፋ አትቁረጥ MYPAmh 75

ልባችሁ የጠነከረ ስለመሰላችሁ ተስፋ አትቁረጡ:: እያንዳንዱ እንቅፋት፣ እያንዳንዱ የውስጥ ጠላት ለእናንተ የክርስቶስን አስፈላጊነት ብቻ ይጨምራል። •እርሱ የድንጋይን ልብ ወስዶ የሥጋን ልብ ለመስጠት መጣ። ልዩ የሆኑ ስህተቶቻችሁን ለማሸነፍ እንድትችሉ ልዩ ፀጋ እንዲሰጣችሁ ወደ እርሱ ተመልከቱ። የፈተና ጥቃት ሲደርስባችሁ ክፉ ሀሳቦችን በፅናት ተከላከሉ። ለነፍሳችሁ «አዳኜን እንዴት አዋርደዋለሁ? ራሴን ለርሱ ሰጥቻለሁ፣ የሰይጣንን ሥራ መስራት አልችል» በሉ። እያንዳንዱን ጣዖት መሰዋት እንድትችሉና እያንዳንዱን የምትወዱትን ኃጢአት ማስወገድ እንድትችሉ እንዲረዳችሁ ወደ ውድ አዳኛችሁ ጩሁ። የእምነት አይናችሁ ኢየሱስ በአባቱ ዙፋን ፊት ቆሞ ለእናንተ በመለመን የቆሰሉ እጆቹን ሲያሳይ ይመልከቱ። ብርታት የሚመጣላችሁ በውድ አዳኛችሁ አማካይነት መሆኑን እመኑ። MYPAmh 75.6