Go to full page →

ክርስቶስን ማሰላሰል። MYPAmh 76

በእምነት ለሚያሸ”ፉ የተዘጋጀላቸውን ዘውድ ተመልከቱ። የታረደውና ለአባታችን ያዳነን በግ ይገባዋል የሚለውን የዳኑት የሚዘምሩትን የከበረ መዝሙር ስሙ። እነዚህን ሁኔታዎች እንደ እውነተኛ ክስተቶች ለማየት ሞክሩ። የመጀመሪያው ክርስቲያን ሰማዕት የነበረው እስጢፋኖስ ከገዥዎችና ኃይላት እንዲሁም በከፍታ ሥፍራ ካሉ መንፈሳዊ እርኩሰት ጋር በነበረው አስከፊ ጦርነት የዓለም አዳኝ ከሰማይ ወደ ታች ጥልቅ በሆነ ፍላጎት እየተመለከተ ታየው። ከክርስቶስ ፊት የሚወጣው ባለ ግርማ ብርሃን በእስጢፋኖስ ፊት ላይ በርቶ ጠላቶች እንኳን ፊቱ እንደ መልአክ ፊት ሲበራ ተመለከቱ። MYPAmh 76.1

አእምሮአችን በክርስቶስና በሰማያዊ ነገሮች ላይ እንዲያርፉ ከፈቀድን የጌታን ጦርነት ስንዋጋ ሃይለኛ ማነቃቂያ ድጋፍ እናገኛለን። በቅርቡ አገራችን ሊሆን ስላላው የተሻለ አገር ክብር ማሰላሰል ስንጀምር ኩራትና የዓለም ፍቅር ኃይላቸውን ያጣሉ። ከክርስቶስ ውበት ውጭ የሆነ ሌላ ምድራዊ ብልጭልጭ ሁሉ ዋጋ ቢስ ይመስላል። MYPAmh 76.2