Go to full page →

የኃይል ምስጢራዊ ቦታ MYPAmh 78

ሰዎች ዛሬም ሆነ ድሮ የሚጠገኑት ሁሉን ቻይ በሆነው ጥላ ሥር በኃይሉ የምስጢር ቦታ ነው። በዚህ ቦታ ለአንድ ወቅት ይቆዩና በሕይወታቸው የከበሩ ተግባራት ተፈፅመው ይታያሉ። ሆኖም እምነታቸው ሲደክም፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያላቸው ግንኙነት ሲቋረጥ የሕይወት ስራቸው ይበላሻል። ነገር ግን የክርስቶስ ሕይወት ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር በሚደረግ ግንኙነት የተደገፈ የማይለዋወጥ የመታመን ሕይወት ነበር። ለሰማይና ለምድር የነበረው አገልግሎትም ስኬታማ ነበር። MYPAmh 78.2

እንደ ሰው፣ ሰብዓዊነቱ ሰብዓዊነትን ከመለኮታዊነት ጋር ካገናኘው ሰማያዊ የኃይል ምንጭ ኃይል እስኪያገኝ ድረስ ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ልመናውን አቀረበ። Education P. 80, 81. MYPAmh 78.3