Go to full page →

የፈተና ዋጋ MYPAmh 78

የሕይወት ፈተናዎች ከባሕሪያችን ውስጥ ቆሻሻንና ሸካራነትን ለማስወገድ የሚያገለግሉ የእግዚአብሔር ሰራተኞች ናቸው። የእነርሱ መቁረጥ፣ ቅርፅ ማውጣት፣ በመሮ መጥረብ ፣መሞረድና መቦረሽ የሚያሳምም ሂደት ነው። በወፍጮ መጨፍለቅ ከባድ ነው። ነገር ግን ከዚህ ሂደት በኋላ ድንጋዩ በሰማያዊው ቤተመቅደስ ቦታውን ለመያዝ ብቁ ሆኖ ይወጣል። ጌታ ይህንን የመሰለ ጥንቃቄና ትኩረት ያለበትን ሥራ የሚሰራው በማይጠቅም ነገር ላይ አይደለም:: በቤተ መንግሥት አምሳያነት ተሞርደው እንዲለሰልሱ የተደረጉት የእርሱ የከበሩ ድንጋዮች ብቻ ናቸው። Thought from the mount of Blesing P. 23, 24. MYPAmh 78.1