Go to full page →

ፀንቶ ለመቆም እድገት አስፈላጊ ነው። MYPAmh 82

የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ለመሆን በወሰነ በእያንዳንዱ ወጣት ልብ ውስጥ ከፍ ወዳለው የክርስትና ደረጃ ለመድረስ “ከክርስቶስ ጋር አብሮ ለመስራት ልባዊ ፍላጎት ሊኖር ይገባል። ዓላማ ካለው ያለማቋረጥ ወደ ፊት መቀጠል ያስፈልገዋል። ፀንቶ ለመቆም ብቸኛው መንገድ በየእለቱ በመለኮታዊ ሕይወት ለውጥ ማሳየት(ማደግ) ነው። እምነት የሚያድገው ከጥርጣሬና ከእንቅፋቶች ጋር በመዋጋት አሸናፊ ሆኖ ሲገኝ ነው። እውነተኛ ቅድስና እድገት የሚያሳይ ነው። በኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋና እውቀት •እያደግክ ከሆነ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወትና ባህሪይ የበለጠ እውቀት ለማግኘት እያንዳንዱን እድልና አጋጣሚ ትጠቀምበታለህ ። MYPAmh 82.2

በኢየሱስ ያለህ እምነት የሚያድገው በእንከን የለሽ ሕይወቱና ዘላለማዊ በሆነው ፍቅሩ በማረፍ ከአዳኝህ ጋር በተሻለ ሁኔታ ስትተዋወቅ ነው። ከምንም የበለጠ የእግዚአብሔርን ክብር ዝቅ የምታደርገው የእርሱ ደቀ መዝሙር ነኝ እያልክ ከእርሱ ርቀህ በመንፈስ ቅዱስ ሳትመገብና ሳትለመልም ስትቀር ነው። በፀጋ እያደግክ ስትሄድ መንፈሳዊ ስብሰባዎችን ለመካፈል ትወዳለህ፣ የክርስቶስን ፍቅር በሕዝብ ፊት ለመመስከርም ደስተኛ ትሆናለህ። እግዚአብሔር በፀጋው ወጣቱን ቀና ያደርገዋል፤ ለልጆቹም እውቀትና ልምድ ይሰጣቸዋል። በየቀኑ በፀጋ ያድጋሉ። እምነትህን በስሜትህ መለካት የለብህም። MYPAmh 82.3