Go to full page →

ራስን መቆጣጠር MYPAmh 90

«ለቁጣ የዘገየ ሰው ከብርቱ ይሻላል፣ መንፈሱን የሚገዛም ከተማን ከሚገዛ ይሻላል፡፡» እንዲህ ዓይነት ሰው የሰው ልጅን ሊያገኙ ከሚችሉ ጠላቶች ሁሉ ብርቱ የሆነውን ጠላት አሸንፎአል፡፡ MYPAmh 90.1

በክርስቲያን ሕይወት የባህርይ መልካምነት ትልቁ ማረጋገጫ እራስን መቆጣጠር ነው፡፡ በበደል ማእበል መካከል ሳይናወጥ የሚቆም ከእግዚአብሔር አሸናፊዎች አንዱ ነው፡፡ MYPAmh 90.2

መንፈስን መግዛት ማለት እራስን መቆጣጠር መቻል ማለት ነው፤ ክፉን መቋቋም ማለት ነው፤ እያንዳንዱን ቃልና ተግባር በእግዚአብሔር ታላቁ የጽድቅ መስፈርት መቆጣጠር ማለት ነው፡፡ መንፈሱን መግዛትን የተማረ ሰው በየእለቱ ከሚገጥሙት ከውርደት፣ ፌዝና ከሚያውኩ ነገሮች በላይ ከፍ ብሎ ይነሳና እነዚህ ነገሮች በመንፈሱ ላይ ሀዘን ማሳረፍን ያቆማሉ፡፡ MYPAmh 90.3

በእግዚአብሔር ፀጋ ቁጥጥር ስር የዋለ የተቀደሰ የአእምሮ ግንዛቤ ንጉሳዊ ኃይል በሰዎች ሕይወት ላይ ተፅእኖ እንዲኖረው የእግዚአብሔር እቅድ ነበር፡፡ መንፈሱን የሚገዛ ይህ ኃይል አለው፡፡ MYPAmh 90.4