Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ራስን መቆጣጠር

    «ለቁጣ የዘገየ ሰው ከብርቱ ይሻላል፣ መንፈሱን የሚገዛም ከተማን ከሚገዛ ይሻላል፡፡» እንዲህ ዓይነት ሰው የሰው ልጅን ሊያገኙ ከሚችሉ ጠላቶች ሁሉ ብርቱ የሆነውን ጠላት አሸንፎአል፡፡MYPAmh 90.1

    በክርስቲያን ሕይወት የባህርይ መልካምነት ትልቁ ማረጋገጫ እራስን መቆጣጠር ነው፡፡ በበደል ማእበል መካከል ሳይናወጥ የሚቆም ከእግዚአብሔር አሸናፊዎች አንዱ ነው፡፡MYPAmh 90.2

    መንፈስን መግዛት ማለት እራስን መቆጣጠር መቻል ማለት ነው፤ ክፉን መቋቋም ማለት ነው፤ እያንዳንዱን ቃልና ተግባር በእግዚአብሔር ታላቁ የጽድቅ መስፈርት መቆጣጠር ማለት ነው፡፡ መንፈሱን መግዛትን የተማረ ሰው በየእለቱ ከሚገጥሙት ከውርደት፣ ፌዝና ከሚያውኩ ነገሮች በላይ ከፍ ብሎ ይነሳና እነዚህ ነገሮች በመንፈሱ ላይ ሀዘን ማሳረፍን ያቆማሉ፡፡MYPAmh 90.3

    በእግዚአብሔር ፀጋ ቁጥጥር ስር የዋለ የተቀደሰ የአእምሮ ግንዛቤ ንጉሳዊ ኃይል በሰዎች ሕይወት ላይ ተፅእኖ እንዲኖረው የእግዚአብሔር እቅድ ነበር፡፡ መንፈሱን የሚገዛ ይህ ኃይል አለው፡፡MYPAmh 90.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents