Go to full page →

በተግባር የተደገፈ እውቀት ያስፈልጋል። MYPAmh 93

ወጣቶች ከዓለም ጋር በተግባርና በመንፈስ የሚያስተሳስራችሁን ቀጭኑን ክር እንድትቆርጡት እማፀናችኋለሁ። “ከመካከላቸው ውጡ፣ ተለዩ፣ እርኩስ ነገርን አትንኩ። እኔም እቀበላችኋለሁ፣ አባትም እሆናችኋለሁ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ ይላል ሁሉን ቻይ አምላክ።” MYPAmh 93.3

ወጣቶች ለዚህ የግብዣ ድምፅ ጆሮአቸውን ይሰጡ ይሁን? በወጣት ጓደኞቻቸው ፊት በሕይወትና በባሕሪይ ክርስቶስን የሚመስል ምሳሌ የማሳየት አስፈላጊነትን የሚገነዘቡ ወጣቶቻችን ምንኛ ጥቂት ናቸው! አብዛኞቹ ወጣቶቻችን የእውነትን ጽንሰ ሀሳብ ያውቃሉ፤ ነገር ግን ተግባራዊ እውነትን በእያንዳንዱ ድርጊታቸው የመግለፅ ተግባራዊ እውቀት ያላቸው ምንኛ ጥቂት ናቸው! በታላቁ የመከር መስክ ራሳቸውን የሚገልጽ ማንኛውንም ሥራ የሚሰሩ ወጣት ሚስዮናውያን የት ናቸው? በየቀኑ በኢየሱስ ት/ቤት የሚማሩ የት ናቸው? በፍፁም ለመመረቅ እንደተዘጋጁ አይሰማቸውም ። ከሰማያዊ ኃይላት ጋር በመተባበር እንዴት መሥራት እንደሚችሉ መመሪያ እስኪሰጣቸው ድረስ በጌታ ፊት ይጠብቁ። ውድ ወጣቶች ሆይ! እንድታድጉ ስለምፈልግ በቀጥታ ልናገራችሁ እሻለሁ። ጊዜያችሁን አታባክኑ። እግዚአብሔርንና ገንዘብን ማገልገል አትችሉም። ክርስቲያኖች መሆን ትችላላችሁ፣ ነገር ግን ፈተናዎች ሲመጡና በብርቱ ስትፈተኑ ትሸነፋላችሁን? MYPAmh 93.4