Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በተግባር የተደገፈ እውቀት ያስፈልጋል።

    ወጣቶች ከዓለም ጋር በተግባርና በመንፈስ የሚያስተሳስራችሁን ቀጭኑን ክር እንድትቆርጡት እማፀናችኋለሁ። “ከመካከላቸው ውጡ፣ ተለዩ፣ እርኩስ ነገርን አትንኩ። እኔም እቀበላችኋለሁ፣ አባትም እሆናችኋለሁ እናንተም ወንዶችና ሴቶች ልጆቼ ትሆናላችሁ ይላል ሁሉን ቻይ አምላክ።”MYPAmh 93.3

    ወጣቶች ለዚህ የግብዣ ድምፅ ጆሮአቸውን ይሰጡ ይሁን? በወጣት ጓደኞቻቸው ፊት በሕይወትና በባሕሪይ ክርስቶስን የሚመስል ምሳሌ የማሳየት አስፈላጊነትን የሚገነዘቡ ወጣቶቻችን ምንኛ ጥቂት ናቸው! አብዛኞቹ ወጣቶቻችን የእውነትን ጽንሰ ሀሳብ ያውቃሉ፤ ነገር ግን ተግባራዊ እውነትን በእያንዳንዱ ድርጊታቸው የመግለፅ ተግባራዊ እውቀት ያላቸው ምንኛ ጥቂት ናቸው! በታላቁ የመከር መስክ ራሳቸውን የሚገልጽ ማንኛውንም ሥራ የሚሰሩ ወጣት ሚስዮናውያን የት ናቸው? በየቀኑ በኢየሱስ ት/ቤት የሚማሩ የት ናቸው? በፍፁም ለመመረቅ እንደተዘጋጁ አይሰማቸውም ። ከሰማያዊ ኃይላት ጋር በመተባበር እንዴት መሥራት እንደሚችሉ መመሪያ እስኪሰጣቸው ድረስ በጌታ ፊት ይጠብቁ። ውድ ወጣቶች ሆይ! እንድታድጉ ስለምፈልግ በቀጥታ ልናገራችሁ እሻለሁ። ጊዜያችሁን አታባክኑ። እግዚአብሔርንና ገንዘብን ማገልገል አትችሉም። ክርስቲያኖች መሆን ትችላላችሁ፣ ነገር ግን ፈተናዎች ሲመጡና በብርቱ ስትፈተኑ ትሸነፋላችሁን?MYPAmh 93.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents