አራቱ ወጣት እብራውያን በባቢሎን ንጉሥ ፊት ለመቆም ትምህርት ይማሩ በነበሩበት ወቅት የእግዚአብሔርን በረከት ይጠበቅባቸው ለነበረው ከባድ ሥራ እንደምትክ አልወሰዱም ነበር። በእግዚአብሔር ፀጋ፣ የወደፊት መዳረሻቸው በራሳቸው ፈቃድና ድርጊት የሚወሰን መሆኑን ስላወቁ በትምህርታቸው ትጉህ ነበሩ። የነበራቸውን ችሎታ በሙሉ በሥራ ላይ ማዋል ነበረባቸው። በመጨረሻም የነበሩአቸውን ኃይሎች በሙሉ ጥብቅ በሆነ ሥራ ላይ በማዋል ለትምህርትና ለሥራ የተሰጡአቸውን እድሎች አሟጥጠው መጠቀም ነበረባቸው:: MYPAmh 98.1