Go to full page →

ከሙሉ ልብ የሚደረግ አገልግሎት MYPAmh 98

ወጣቶች ሆይ •ታማኝ ሁኑ እላችኋለሁ። ልባችሁን በሥራችሁ ላይ አድርጉ። ሰነፎችንና የተከፋፈለ አገልግሎት የሚሰጡትን አትኮርጁ። ብዙ ጊዜ የሚደጋገሙ ድርጊቶች ልማድ ይሆናሉ፣ ልማዶች ደግሞ ባህሪይን ይመሠርታሉ። በትዕግሥት ትናንሽ የሕይወት ተግባራትን ፈጽሙ። በእነዚህ ትናንሽ ተግባራት ላይ ሊኖር ለሚገባው ታማኝነት ዝቅተኛ ቦታ የምትሰጡ ከሆነ የባህሪይ ግንባታችሁ አጥጋቢ አይሆንም። ሁሉን በሚችለው እይታ እያንዳንዱ ተግባር አስፈላጊ ነው። ጌታ “በጥቂት የታመነ በብዙም የታመነ ይሆናል” ብሏል። በእውነተኛ ክርስቲያን ሕይወት ዝቅተኛ የሚባሉ ተግባራት የሉም። MYPAmh 98.4

ብዙዎች ክርስቲያን ነን ባዮች ከእግዚአብሔር ጋር በመንታ ዓላማ አብረው እየሰሩ ናቸው። ብዙዎች የሆነ ታላቅ ሥራ እንዲመጣላቸው እየጠበቁ ነው። በየእለቱ ለእግዚአብሔር ታማኝነታቸውን የማሳየት እድላቸውን ያጣሉ። በየዕለቱ ደስ የማይሉ የሚመስሉትን ትናንሽ ተግባራት ከሙሉ ልብ የመፈፀም ኃላፊነታቸውን ሳይወጡ እየቀሩ ናቸው። አሉን የሚሉአቸውን ታላላቅ መክሊቶቻቸውን ሥራ ላይ የሚያውሉበትን •ታላቅ ሥራ የጠበቁና ዓለማዊ ምኞታቸውን ለማርካት እየፈለጉ ያሉ ሕይወታቸው ያልፋል፡፡ MYPAmh 98.5

ውድ ወጣት ወዳጆች ሆይ! በአጠገባችሁ ያለውን ሥራ ሥሩ። ልትዳርስ በምትችልበት ቦታ ወዳለው ዝቅተኛ ሥራ ትኩረትህን መልስ። በዚህ ሥራ ላይ አእምሮህንና ልብህን አሳርፍ። አስተሳሰቦችህን በቤትህ ልታደርግ የምትችላቸውን ነገሮች በማስተዋል ለማድረግ አስገድድ። ያኔ ራስህን ለትልቅ ጠቀሜታ ገጣሚ እያደረግክ ነህ። ስለ ንጉሡ ሕዝቅያስ እንደሚከተለው እንደተፃፈ አስታወስ። “የጀመረውን እያንዳንዱን ሥራ በሙሉ ልቡ ሠራው፣ ተከናወነለትም።” MYPAmh 99.1