Go to full page →

ትኩረት የመስጠት ጠቀሜታ MYPAmh 99

በእጃችን ባለው ሥራ ላይ የማተኮር ችሎታ ታላቅ በረከት ነው። እግዚአብሔርን የሚፈሩ ወጣቶች አስተሳሰባቸውን በትክክለኛው መስመር በመጠበቅና የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ኃላፊነቶቻቸውን (የተሰጣቸውን ሥራ) ትኩረት በመስጠት ለመፈፀም መጣር አለባቸው። አሁን በእጃቸው ያሉትን ተግባራት መገንዘብና አእምሮአቸው እንዲባዝን ባለመፍቀድ መፈፀም አለባቸው። አእምሮን በዚህ መልክ ማሰልጠን በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ይጠቅማቸዋል። በሚያደርጉት በእያንዳንዱ ነገር ላይ ተገቢ የሆነ ትኩረት መስጠትን የሚማሩ ሥራው ምንም ያህል ትንሽ ቢመስልም በዓለም ላይ ጠቃሚ ሰዎች ይሆናሉ። MYPAmh 99.2

ውድ ወጣቶች! የምትተጉና የማትደክሙ ሁኑ። “የአእምሮአችሁን ወገብ ታጠቁ።” በልቡ ለእግዚአብሔር እውነተኛ ለመሆን እንደ ወሰነው እንደ ታማኙ ዕብራዊ ዳንኤል ቁሙ። ወላጆቻችሁንና ጓደኞቻችሁን ተስፋ አታስቆርጡአቸው። ሌላም ማስታወስ የሚገባችሁ ነገር አለ። ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ ሠራተኛ መሆን እንድትችሉ ለማድረግ ሕይወቱን እስከ መስጠት ድረስ የወደዳችሁን ጌታ አታሳዝኑት። MYPAmh 99.3