Go to full page →

በፍቅሩ መሠራት MYPAmh 105

አእምሮ በክርስቶስ ላይ ሲያርፍ ባህሪይ በመለኮታዊ አምሳያ ይሠራል። ሀሳቦች በእርሱ መልካምነትና ፍቅር ይሞላሉ። ባህሪዩን ስለምናሰላስል ሀሳባችን ሁሉ ስለ እርሱ ይሆናል፤ ፍቅሩ ይሸፍነናል። አስደናቂ የሆነውን የፀሐይን ክብር ለአፍታ እንኳን ከተመለከትን በኋላ ዓይናችንን ወደ ሌላ አቅጣጫ ብናዞር የፀሐዩ ምስል በእያንዳንዱ በምናየው ነገር ላይ ይታያል። MYPAmh 105.4

ኢየሱስንም ስናይ እንደዚሁ ነው የሚሆነው:: የምናየው ነገር ሁሉ የጽድቅ ፀሐይ የሆነውን የእርሱን ምስል ያንፀባርቅልናል። ከእርሱ በቀር ምንም ሌላ ነገር ማየት ወይንም ስለ ማንኛውም ሌላ ነገር መናገር አንችልም። የእርሱ ምስል በነፍስ ዓይን ላይ ስለተፃፈ የዕለታዊ ሕይወታችንን እያንዳንዱን ክፍል በመንካት፤ ጠቅላላ ተፈጥሮአችንን በማለስለስና በማስገዛት ይሰራል። በመመልከት ወደ መለኮታዊው አምሳል ያውም ወደ ክርስቶስ አምሳያነት እንለወጣለን። ግንኙነት ላለን ሰዎች በሙሉ የጽድቁን ብሩህና አስደሳች ጮራዎች እናንፀባርቃለን። ልብ፣ ነፍስና አእምሮ በወደደንና ራሱን ለእኛ በሰጠው በእርሱ ነፀብራቅ ስለ በሩ ባህሪያችን ተለውጧል። እዚህም በድጋሚ ግላዊ የሆነ ህያው ተፅእኖ በእምነት በልባችን ማደሩን እንረዳለን። MYPAmh 105.5

እርሱ የሚያስተምረን ቃሎች ተቀባይነት ሲያገኙና እኛን ሲቆጣጠሩን ኢየሱስ ሐሳባችንን፣ አስተሳሰባችንንና ተግባራችንን በመቆጣጠር በውስጣችን ይኖራል። ዓለም አይቶአቸው ከሚያውቃቸው መምህራን ሁሉ ታላቁ በሆነው መምህር ትምህርት የተሞላን እንሆናልን። የሰብዓዊ ተጠያቂነትና ተፅዕኖ ስሜት ለሕይወት አመለካከታችንና ስለ ዕለታዊ ተግባሮቻችን መልክ ይሰጣል። ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኛ ሁሉም ነገር ነው። እርሱ የመጀመሪያ፣ የመጨረሻ፣ ከሁሉም ነገር የተሻለ ነው። MYPAmh 105.6

ኢየሱስ ክርስቶስ ባሕሪዩ፣ መንፈሱ፣ ሁሉን ነገር ያዳምቀዋል። እርሱ ድርና ማግ፣ የአጠቃላይ ማንነታችን ውበት ነው። የክርስቶስ ቃላት መንፈስና ሕይወት ናቸው። ስለዚህ ሐሳቦቻችንን በራሳችን ላይ ማተኮር አንችልም። የምንኖረው እኛ ሳንሆን ክርስቶስ በእኛ ውስጥ ነው። እርሱ የክብር ተስፋ ነው። ራስ ሙቷል፤ ነገር ግን ክርስቶስ ህያው አዳኝ ነው። ክርስቶስን ማየታችንን ስንቀጥል በዙሪያችን ላሉ ሁሉ የእርሱን ምስል እናንፀባርቃለን። ያጋጠሙንን ተስፋ መቁረጦች አናስባቸውም ወይም ስለ እነርሱ አናወራም፡፡ ለዚህም ምክንያቱ የበለጠ ማራኪ ስዕል ያውም የክርስቶስ ፍቅር እይታችንን ስለሚስብ ነው። እርሱ በእውነት ቃሉ በውስጣችን ያድራል። Testimonies to Ministers, P 387-390. MYPAmh 106.1