Go to full page →

እግዚአብሔር የሚያረጋግጠው ባሕርይ MYPAmh 108

ወጣቶች ባሕርያቸውን በነበረው ፅኑ መሰረት ላይ እንዲገነቡ በጥንቃቄና በፀሎት ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል። ብዙዎች አሳዛኝ የሆነ ማጭበርበር የሚፈጽሙበት ምክንያት የልምምድ ትምህርትን ስለማያዳምጡ ነው። የወላጆችና የመምህራን ምክር በእነርሱ ዘንድ ዋጋ ስላጣ ለጠላት ፈተና እጅ ይሰጣሉ። እግዚአብሔር ወጣቶችን ይወዳል። የክርስቶስን አስፈላጊነት የሚገነዘቡ ከሆነና በእርግጠኛ መሠረት ላይ የሚገነቡ ከሆነ በወጣቶች ውስጥ ለመልካም የሚሆኑ ታላላቅ አጋጣሚዎችን ያያል። ደግሞም ፈተናቸውን ያውቃል። የሰውን አእምሮ ለመቆጣጠር የሚጥሩ የጨለማ ኃይላትን መዋጋት እንዳለባቸውም ያውቃል። ወጣት ወንዶችና ሴቶች የመለኮታዊ ባሕሪይ ተካፋዮች መሆን የሚችሉበትን መንገድም ከፍቶላቸዋል። MYPAmh 108.1