Go to full page →

በትዕግሥት የተሞላ ጥረት ያስፈልጋል MYPAmh 108

ባሕሪይ በእድል አይመጣም። በአንድ የቁጣ መገንፈል አይወሰንም! ወይም በስህተት አቅጣጫ በሚደረግ አንድ እርምጃ አይወሰንም:: ልማድ እንዲሆን የሚያደርግ ተግባርን በመደጋገም የሚመጣና ባህሪይን ለክፉ ወይም ለመልካም የሚቀርፅ ነው። መልካም ባህሪዮች የሚመሰረቱት በትዕግስት በተሞላና መሰልቸት በሌለበት ጥረት የተሰጡንን መክሊቶችና ችሎታዎች ለእግዚአብሔር ክብር በማሻሻል ነው። ይህንን በማድረግ ፈንታ ብዙዎች ስሜታቸው ወይንም ሁኔታዎች ወደ ወሰዱአቸው አቅጣጫ ለማፈንገጥ ይፈቅዳሉ። ይህ የሚሆንበት ምክንያት መልካም ነገር ስለላቸው ሳይሆን በወጣትነት ጊዜያቸው ከሁሉ የተሻለ ነገር እንዲሰሩ እንደሚፈልግባቸው ስለማይገነዘቡ ነው። MYPAmh 108.2

የዛሬ ወጣቶች ዳንኤል እንደቆመ ፀንተው መቆም ካለባቸው እያንዳንዱን መንፈሳዊ ነርቭና ጡንቻ ሥራ ላይ ማዋል አለባቸው። ጌታ አዲስ አማኞች (ጀማሪዎች) ሆነው እንዲቀሩ አይሻም። እርሱ የሚሻው እጅግ ከፍ ወዳለው የብቃት ደረጃ እንዲደርሱ ነው። እርሱ የሚሻው ወደ መሰላሉ ጫፍ በመድረስ ከዚያ ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዲሸጋገሩ ነው። MYPAmh 108.3