Go to full page →

የክርስቶስ መገኘት MYPAmh 110

የክርስቶስ ሐይማኖት ማለት ከኃጢአት ይቅርታ የበለጠ ነው፡፡ ኃጢአታችንን ማስወገድና ባዶ ቦታውን በመንፈስ ቅዱስ ፀጋዎች መሙላት ማለት ነው፡፡ በመለኮታዊ ብርሃን፣ በእግዚአብሔር መደሰት ማለት ነው፡፡ ልብ ከራስ ወዳድነት መጽዳትና በክርስቶስ መገኘት መባረክ ማለት ነው፡፡ ክርስቶስ በነፍስ ውስጥ ሲነግስ ንጽህናና ከኃጢአት ነፃ መውጣት አለ፡፡ የወንጌል እቅድ ክብር፣ ሙላትና ፍጽምና በህይወት ውስጥ ይፈፀማል፡፡ አዳኙን መቀበል ፍፁም ሰላም፤ ፍቅር፣ እርግጠኝነትና ግለት ያመጣል፡፡ የክርስቶስ ባሕርይ ውበትና መልካም መዓዛ በሕይወት ውስጥ ሲገለጽ በርግጥ እግዚአብሔር ለዓለም አዳኝ እንዲሆን ልጁን የመላኩ ማረጋገጫ ይሆናል፡፡ MYPAmh 110.1

ክርስቶስ ለታማኝ ተከታዮቹ የየእለቱ ወዳጃቸውና የቅርብ ጓደኛቸው ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር በቅርበትና ሁል ጊዜ እየተገናኙ ኖረዋል፡፡ በላያቸው የጌታ ክብር ወጥቶላቸዋል፡፡ በእነርሱ ውስጥ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን ክብር የማወቅ ብርሃን ተንፀባርቋል፡፡ አሁን በንጉሱ ባልደበዘዘ ጮራዎችና በክብሩ ብሩህነት ይደሰታሉ፡፡ ሰማይ በልቦቻቸው ውስጥ ስላለ ከሰማይ ጋር ለመገናኘት ተዘጋጅተዋል፡፡ Christ’s Object Lessons, p. 419-421. MYPAmh 110.2