Go to full page →

ክፍል 5—ለሕይወት ሥራ መዘጋጀት MYPAmh 111

እውነተኛ ትምህርት ማለት አንዳንድ ኮርሶችን ከመውሰድ ያለፈ ነገር ነው፡፡ ሰፊ ነው፡፡ የአካል ኃይሎችንና የአእምሮ ችሎታዎችን በአንድነት ማሳደግን ያጠቃልላል፡፡ እግዚአብሔርን መውደድንና ፈርሃ - እግዚአብሔርን ያስተምራል፡፡ እውነተኛ ትምህርት የህይወት ተግባራትን በታማኝነት ለማከናወን መዘጋጀት ነው፡፡ Counsels to Teachers, Parents and Students, p.64. MYPAmh 111.1

እውነተኛ ትምህርት የአካል ፣ የአእምሮና የሞራል ኃይሎችን እያንዳንዱን ተግባር ለመፈፀም ማዘጋጀት ነው፡፡ አካልን፣ አእምሮንና ነፍስን ለመለኮታዊ አገልግሎት ማሰልጠን ነው፡፡ — Christ’s Object Lessons, 330 MYPAmh 111.2