Go to full page →

እንዴት ምግብን ማብሰል እንደምትችሉ ተማሩ MYPAmh 118

ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ወጣቶቻችን ወጪ ቆጣቢ የሆነ የምግብ አበሳሰልንና ከሥጋ ምግብ ጋር ግንኙነት ያለውን ነገር ሁሉ መተውን መማር አለባቸው፡፡ የሥጋ ምግብ የጤና ተሃድሶ ንጽህናን በመቃወም የግብፅን ጨለማና ድንቁርና የሚያሳይ ስለሆነ በየትኛውም መጠን ቢሆን የሥጋ ምግብን እንዲያዘጋጁ መደፋፈር የለባቸውም፡፡ MYPAmh 118.4

በተለይም ሴቶች የምግብ አበሳሰልን ይማሩ፡፡ ለሴት ልጅ ከሚሰጥ ትምህርት ሁሉ ከዚህ የበለጠ ጠቃሚ የሆነ ነገር ምን አለ? በሕይወት ውስጥ በየትኛውም አይነት ሁኔታ ብትሆን በተግባር ላይ ልታውለው የምትችለው ትምህርት ይህ ነው፡፡ MYPAmh 118.5