Go to full page →

በሕይወት ማድረግ የሚቻለውን ሁሉ ማድረግ MYPAmh 127

ጥሩ ትምህርት ከቅድስና ጋር ሲዋሀድ ታላቅ ጥቅም ያለው ቢሆንም እንኳን ከፍተኛ የሆነ የትምህርት እውቀትን ለማግኘት እድሉ ያልነበራቸው ሰዎች በእውቀትና በመንፈሳዊ ህይወት ወደ ፊት መቀጠል እንደማይችሉ ማሰብ የለባቸውም፡፡ ያላቸውን እውቀት በትክክል ሥራ ላይ ቢያውሉት፣ በየቀኑ ወደ ጎተራቸው አንድን ነገር ለመሰብሰብ ቢፈልጉና ክርስቶስን መሰል ባሕርያትን ተግተው ቢያሳድጉ እግዚአብሔር የጥበብ ቦዮችን ይከፍትላቸውና ለጥንቶቹ የእብራውያን ልጆች እንደተባለላቸው ሁሉ ለእነርሱም «እግዚአብሔር ጥበብና ማስተዋል ሰጣቸው» ይባልላቸዋል፡፡ Fundamentals of Christian Education, P. 192-193. MYPAmh 127.4