Go to full page →

ንግግራችን MYPAmh 132

የዘመኑ ተለዋዋጭ የሆነ ሃይማኖት በክርስቶስ እናምናለን የሚሉ ወጣቶች አብረዋቸው ለሚሆኑ ሰዎች ስሙን እንኳን እስከማያነሱ ድረስ ባሕርይን አበላሽቷል፡፡ ስለ ብዙ ነገሮች ይነጋገራሉ፣ ነገር ግን የደህንነት ክቡር እቅድ የንግግራቸው ዋና ሐሳብ አልሆነም፡፡ ተግባር እንዳላቸው ክርስቲያኖች የእነዚህን ነገሮች ቅደም ተከተል በመቀየር «ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን የጠራችሁን የእርሱን በጎነት ለመግለጽ” ማሰብ አለባችሁ፡፡ ክርስቶስ በእምነት በልባችሁ ውስጥ ካደረ ዝም ማለት አትችሉም፡፡ ኢየሱስን አግኝታችሁ ከሆነ እውነተኛ ሚስዮናውያን መሆን ትችላላችሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ልባዊ ግለት ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ ለኢየሱስ አድናቆት የሌላቸው ሰዎች እርሱን ለነፍሳችሁ የከበረ ሆኖ እንዳገኛችሁት፣ በአፋችሁ አዲስ ዝማሬ ማለትም ለእግዚአብሔር ምስጋና እንዳስቀመጣችሁ ይወቁ፡፡ MYPAmh 132.2

ወጣት ወዳጆቼ፣ የክርስትና ህይወታችሁን ልባቸው በኢየሱስ ፍቅር እንደሞቀ ሰዎች ትጀምራላችሁን? የእግዚአብሔር ልጅነት እንደሚገባቸው ለማይሰማቸው ሰዎች በትህትና የተሞሉ ትርጉም ያላቸውን ቃላት በመናገር ምን ያህል ጥሩ ነገር እንደምታደርጉ በፍፁም አታውቁም፡፡ በሌላው በኩል የክርስቶስ ምስክሮች ለመሆን የሚያስችሉአችሁን ምን ያህል አጋጣሚዎች ሳትጠቀሙ እንደቀራችሁ እስከ ፍርድ ቀን ድረስ በፍፁም አታውቁም፡፡ ከቅዱስ እምነታችሁ ጋር በማይጣጣም መልኩ በትናንሽ የከንቱነት ተግባሮቻችሁ፣ ርካሽ ንግግሮቻችሁና ቀልደኝነታችሁ በአንዳንድ ነፍሳት ላይ የፈፀማችሁትን ማታለል በዚህ ዓለም ላይ በፍፁም ላታውቁ ትችላላችሁ፡፡ MYPAmh 132.3