Go to full page →

ለክርስቶስ መመስከር MYPAmh 132

ከጌታ ጋር ያሉ ሁሉ ክርስቶስን መመስከር አለባቸው፡፡ ጌታ «እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ” ይላል፡፡ የእውነተኛ አማኝ እምነት በባሕርይ ንጽህናና ቅድስናን ይገለፃል፡፡ እምነት በፍቅር በመስራት ነፍስን ያነፃል፤ ከእምነት ጋርም አብሮ የሚሄድ መታዘዝ እርሱም በታማኝነት የክርስቶስን ቃላት ማድረግ ነው፡፡ ክርስትና ሁል ጊዜ ከእውነታ ህይወት ጋር ከሚገናኙ ሁኔታዎች ጋር ራሱን የሚያለማምድ ጥልቅ ተግባራዊ የሆነ ነገር ነው፡፡ «እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፡፡” ለማን ነው የምንመሰክረው? ምስክሮች የሆንነው ለዓለም ነው፡፡ በዙሪያችሁ ቅዱስ ተጽእኖ ማሳደር አለባችሁ፡፡ ክርስቶስ በነፍሳችሁ ማደር አለበት፡፡ ስለ እርሱ መናገርና የእርሱን ባሕርይ ውበት እንዲገለጥ ማድረግ አለባችሁ፡፡ MYPAmh 132.1