Go to full page →

ልባዊ ትጋት MYPAmh 133

በእግዚአብሔር ሥራ ላይ ሕይወትን ማሳለፍ በረከት ነው፡፡ በጠብ፣ ሥራ-ፈት በሆኑ ቁጭቶችና በማይመቹ ማጉረምረሞች ጊዜያቸውን እያባከኑ ያሉ ሰዎች እግዚአብሔር የሰጣቸውን ብርሃን ቢያደንቁና በሌሎች ላይ እንዲበራ ቢፈቅዱ ኖሮ ሙሉ በሙሉ የተለየ ልምምድ ይሆንላቸው ነበር፡፡ ብዙዎች ህይወትን ጎስቋላ የሚያደርጉት በራሳቸው ራስ ወዳድነትና ምቾት በመሻት ነው፡፡ ሕይወታቸው ትጋት በተሞላበት ሥራ ወደ ሞት በሚያመራው የጨለማ መንገድ ያሉትን ወደ ሰማይ መንገድ ለመምራት እንደ ብሩህ የፀሐይ ጮራ ይሆናል፡፡ ይህንን መንገድ ከተከተሉ ልቦቻቸው በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ደስታ ይሞላሉ፡፡ Review and Herald, October 25,1881. MYPAmh 133.2