Go to full page →

የመጽሐፍ ቅዱስ ሥራ MYPAmh 144

መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናት ሐሳብ ከሰማይ የመነጨ ሐሳብ ስለሆነ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶች በዚህ መንገድ ባይሆን ኖሮ ሊሰራ የማይቻል ጠቃሚ የሆነ የሥራ መስክ ይከፍትላቸዋል፡፡ MYPAmh 144.4

መጽሐፍ ቅዱስ ተፈትቷል፡፡ ወደ ማንኛውም ሰው በር ሊወሰድና በውስጡ ያለው እውነትም ለማንኛውም ሰው ህሊና ሊቀርብ ይችላል፡፡ ዛሬም እንደ ከበሩ የቤሪያ ሰዎች እውነቱ ሲነገራቸው ነገሩ እንደዚያ መሆኑን ለማወቅ መጽሐፍትን በየቀኑ የሚመረምሩ ብዙዎች አሉ፡፡ ክርስቶስ «መጽሐፍትን እሹ ፣ በእርሱ የዘላለም ሕይወት የሚገኝ ይመስላችኋል፡፡ እነርሱ ግን ስለ እኔ የሚናገሩ ናቸው፡፡” ብሏል፡፡ የዓለም መድህን የሆነው ኢየሱስ ሰዎችን መጽሐፍትን እንዲያነቡ ብቻ ሳይሆን እንዲመረምሩ ጭምር ያሳስባቸዋል፡፡ ይህ ታላቅና ጠቀሚ የሆነ ሥራ ነው፣ እንድናደርገው ተሰጥቶናል፣ በማድረጋችንም እጅግ ተጠቃሚዎች እንሆናለን፡፡ ለክርስቶስ ትዕዛዝ ሽልማት አለው፡፡ በቃሉ ውስጥ የተገለጠውን ብርሃን ለመከተል ፈቃደኛ መሆናችን በፊቱ ተቀባይነት ማግኘቱን በሚገልፁ የተለዩ መግለጫዎች ያከብረናል፡፡ Testimonies on Sabbath school Work ,P .29,30. MYPAmh 144.5