Go to full page →

አገልግሎት MYPAmh 146

የወንጌል አገልግሎትን በፍጹም አቅልሎ ማየት አያስፈልግም፡፡ ማንኛውም ሥራ የቃልን አገልግሎት ዝቅተኛ ግምት እንዲሰጠው በሚያደርግ መልኩ መሰራት የለበትም፡፡ እንደዚህም አይደለም፡፡ አገልግሎቱን የሚያቃልሉ ክርስቶስን እያቃለሉ ናቸው፡፡ ከሁሉም ሥራ የሚበልጠው ሥራ በተለያየ መስመር የሚደረግ አገልግሎት ነው፡፡ በወጣቶቻችን ፊት የወንጌል አገልጋይ ከመሆን የበለጠ የተባረከ አገልግሎት እንደሌለ ሊቀመጥ ይገባል፡፡ MYPAmh 146.2

ወጣቶቻችን ወደ አገልግሎት ከመግባት አይራቁ፡፡ አንዳንዶች የጋሉ ሁኔታዎችን በመመልከት እግዚአብሔር እንዲሄዱበት ከሚጠይቃቸው መንገድ የመራቅ አደጋ አለ፡፡ አንዳንዶች ወደ ወንጌል አገልግሎት ለመግባት መዘጋጀት ሲገባቸው በህክምና ዘርፍ እንዲሰለጥኑ የተደፋፈሩ አሉ፡፡ ጌታ በወይኑ ቦታ ላይ የሚሰሩ ብዙ አገልጋዮችን ይፈልጋል፡፡ «ቅጥሩን አጽኑ፣ በዓለም እያንዳንዱ ክፍል ታማኝ ዘቦችን አቁሙ፡፡” የሚሉ ቃላት ተነግረዋል፡፡ ወጣቶች ሆይ፣ እግዚአብሔር ይጠራችኋል፡፡ እርሱ የሚጠራው ትልቅ ልብና ትልቅ አእምሮ ያላቸውንና ለክርስቶስና ለእውነት ጥልቅ ፍቅር ያላቸውን አጠቃላይ የወጣት ሰራዊቶች ነው፡፡ Tesimonies for the Church, vol .6, p 411. MYPAmh 146.3