Go to full page →

የውጭ አገር ሚስዮናዊ MYPAmh 146

ወጣቶች ይፈለጋሉ፡፡ እግዚአብሔር ወደ ሚስዮናዊ የሥራ መስኮች ይጠራቸዋል፡፡ ትልቅ ቤተሰብን የማሰልጠንና የመመገብ ኃላፊነት ካላቸው ጋር ሲነጻጸሩ ከኃላፊነትና ሸክም ከሚሆን ነገር ነጻ ስለሆኑ በሥራ ለመሠማራት የበለጠ ገጣሚ ናቸው፡፡ በተጨማሪም ወጣቶች ከአዲስ የአየር ንብረትና አዲስ ማህበረሰብ ጋር በቀላሉ የመለማመድና ችግሮችንና የማይመቹ ሁኔታዎችን የመቋቋም አቅም አላቸው፡፡ በብልጠትና በመታገስ ሰዎችን ባሉበት መድረስ ይችላሉ፡፡ Tesimonies for the Church, vol.5, P.393. MYPAmh 146.4

እግዚአብሔር እውነትን ለሌሎች ለማስተላለፍ እንደ መሣሪያ እንዲጠቀምባቸው ወጣቶች ከሌሎች ቋንቋዎች ጋር በመተዋወቅ ራሳቸውን ማዘጋጀት አለባቸው፡፡ እነዚህ ወጣቶች ኃጢአተኞችን በማዳን ሥራ ላይ እያሉ እንኳን የሌሎች ቋንቋዎችን እውቀት ማግኘት አለባቸው፡፡ ጊዜያቸውን በአግባቡ የሚጠቀሙ ከሆነ የበለጠ ጠቃሚነት ላለው ሥራ አእምሮአቸውን እያዘጋጁና ራሳቸውን ብቁ እያደረጉ ናቸው፡፡ አነስተኛ ኃላፊነት ያላቸው ወጣት ሴቶች ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ቀድሰው ቢሰጡ ኖሮ ሌሎች ቋንቋዎችን በማጥናትና በመተዋወቅ ራሳቸውን ጠቃሚ ለሆነ ሥራ ገጣሚ ያደርጉ ነበር፡፡ ራሳቸውን ለትርጉም ሥራ ቀድሰው መስጠት ይችላሉ፡፡ Testimonies for the Church, vol.3, p. 204. MYPAmh 147.1