Go to full page →

የተሰጠን የመልካም ዕድል ቀን MYPAmh 29

ባለፉት ትውልዶች ለእግዚአብሔር ከሰሩት ሰዎች ልምድ ዛሬ የምንማራቸው ትምህርቶች አሉ:: እነዚህ ሰዎች የሰይጣንን ሰራዊት ለመግጠም ራሳቸውን ገጣሚ እያደረጉ ሳሉ ካለፉባቸው ተጋድሎዎች፣ ፈተናዎችና ልፋቶች ውስጥ እኛ የምናውቀው በጣም ጥቂቱን ነው:: የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር እቃ በመልበስ የሰይጣንን ማታለያዎች ለመቋቋም ችለዋል …. :: MYPAmh 29.1

እነዚህ በለፉት ጊዜያቶች ለእግዚአብሔርና ሥራውን ከፍ ከፍ ለማድረግ ራሳቸውን የሰጡ ሰዎች ለመርህ እንደ ብረት ጠንካሮች ነበሩ:: ወደኋላ የማያፈገፍጉና ተስፋ የማይቆርጡ ሰዎች ነበሩ:: ልክ እንደ ዳንኤል ለእግዚአብሔር በአክብሮትና ቅንዓት የተሞሉ ነበሩ:: በከበረ ዓላማና ፍላጎት የተሞሉ ነበሩ፡፡ ዛሬ በእግዚአብሔር ሥራ ላይ እንዳሉ ሰዎች ሁሉ እነርሱም ደካማና ረዳተቢስ ነበሩ፤ ነገር ግን ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር የታመኑ ነበሩ፡፡ ሃብት ነበራቸው፣ ግን ሃብታቸው በውስጡ የአእምሮና የነፍስ ሥልጠናን ይዞ ነበር፡፡ እግዚአብሔርን በሁሉም ነገር መጀመሪያ ፣ መጨረሻና ከሁሉም የበለጠ የሚያደርግ እያንዳንዱ ሰው ይህ ይኖረዋል፡፡ ምንም እንኳን ጥበብ፣ እውቀት፣ መልካም ነገርና ኃይል ባይኖረንም እንድንማር በተሰጠን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከክርስቶስ ከተማርን እነዚህ ነገሮች ሁሉ ይሰጡናል፡፡ MYPAmh 29.2