Go to full page →

የሚፈለጉ ዓይነት ሠራተኞች MYPAmh 29

•እኛ ባለፉት ትውልዶች ለማግኘት ቀላል ያልነበሩ እድሎችና ጥቅሞች አሉን፡፡ የበለጠ ብርሃን አለን፣ ይህ ብርሃን የመጣው እግዚአብሔርን መጠጊያቸው ካደረጉና ብርሃን ግልጽና ብሩህ በሆነ ሁኔታ ለዓለም እንዲበራ ካደረጉ ታማኝ አገልጋዮች ሥራ ነው፡፡ ባለፉት ዘመናት የከበሩ ሰዎች እግዚአብሔር የሰጣቸውን ብርሃን በመጠቀም እንዳሻሻሉት ሁሉ በኛ ጊዜም መሻሻል የሚችል ብዙ ብርሃን አለ፡፡ በክርስቶስ ት/ቤት የሚሰጠውን ትምህርት ለመማር ለረዥም ጊዜ ለፍተዋል፤ ልፋታቸው ግን በከንቱ አልነበረም፡፡ ያልተቆጠበ ጥረታቸው ሽልማት ነበረው፡፡ ከኃይላት ሁሉ በላይ ከሆነው ኃይል ጋር ራሳቸውን ያቆራኙ ቢሆንም በተሳካ ሁኔታ የእውነትን ሃብት ለዚህ ዓለም ለማቅረብ እንዲችሉ ዘላለማዊ እውነታዎችን ለማስተዋል የጠለቀ፣ ከፍ ያለና ሰፊ ማስተዋልን ይናፍቁ ነበር፡፡ MYPAmh 29.3

ዛሬም ይህን የመሰለ ባህሪይ ያላቸው ሠራተኞች ይፈለጋሉ፡፡ በእግዚአብሔር እይታ ሰዎች የሆኑና በሰማይ መጽሐፍት የተመዘገቡ፣ በዚህ በኃጢአት ውስጥ ባለ ዓለም የእግዚአብሔርን መንግስት መወከል እንዲችሉ ልክ እንደ ዳንኤል እያንዳንዱን የተፈጥሮ ሥጦታዎች የሚያሳድጉ ሰዎች ይፈለጋሉ፡፡ በእውቀት ማደግ አስፈላጊ ነው፤ እውቀት በእግዚአብሔር ሥራ ላይ ሲውል የመልካም ነገር ኃይል ነው፡፡ ዓለም ማሰብ የሚችሉ፣ በመርህ የሚመሩ፣ በማስተዋልና በጥበብ ያለ ማቋረጥ የሚያድጉ ሰዎችን ይሻል፡፡ ወንጌልን ለህዝብ፣ ለቋንቋና ለወገን ሁሉ በፍጥነት ለማድረስ እውነት ክንፍ እንዲሰጣት ማተሚያ ቤትን በትክክል መጠቀም የሚችሉ ሰዎች ያስፈልጋሉ፡፡ MYPAmh 29.4