Go to full page →

ለአገልግሎት የሚያነሳሱን እውነተኛ ምክንያቶች MYPAmh 149

ክርስቲያን ነን የሚሉና ከክርስቶስ ጋር አንድ ያልሆኑ ብዙዎች ናቸው፡፡ የየዕለቱ ሕይወታቸውና መንፈሳቸው የክብር ተስፋ የሆነው ክርስቶስ በውስጣቸው እንዳልተመሠረተ ይመሰክራል፡፡ ልንተማመንባቸው አንችልም፡፡ አገልግሎታቸው አነስተኛ ጥረትን እስከሚጠይቅበት ደረጃ ድረስ ዝቅ ለማድረግ ጉጉዎች ሆነው ሳሉ ለአገልግሎታቸው ግን ከፍተኛ ክፍያ ይጠይቃሉ፡፡ «አገልጋይ» የሚለው ስም የሚቆመው ለእያንዳንዱ ሰው ነው፡፡ ሁላችንም አገልጋዮች ስለሆንን ምን ዓይነት ቅርጽ እየያዝን እንዳለን ማየት መልካም ነው፡፡ የአለመታመን ወይስ የታማኝነት ቅርጽ እየያዝን ነን? MYPAmh 149.5

በአጠቃላይ በአገልጋዮች መካከል መሥራት የሚቻለውን ሁሉ መሥራት ዝንባሌያቸው ነውን? በአብዛኛው የሚታየው ፋሽን ሥራን በተቻለ ፍጥነት፣ በቀላሉ፣ በተቻለ መጠን ሰርተው ዋጋቸውን ግን ለራሳቸው አነስተኛ የሆነ ወጪ በማድረግ ማግኘት አይደለምን? ዓላማቸው በተቻለ መጠን ሥራቸውን በደንብ መሥራት ሳይሆን ደሞዝ ማግኘት ነው፡፡ የክርስቶስ አገልጋዮች ነን ባዮች የሐዋሪያው ጻውሎስን ትዕዛዝ መርሳት የለባቸውም፡፡ «ባሪያዎች ሆይ፣ በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑት በሁሉም ነገር ታዘዙአቸው፡፡ ለታይታ ወይም ሰዎችን ለማስደሰት አይሁን፡፡ ነገር ግን በሙሉ ልብ እግዚአብሔርን በመፍራት ይሁን፡፡ የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ ከልባችሁ አድርጉት፡፡ ከጌታ የርስትን ሽልማት እንደምታገኙ በመቁጠር አገልግሉ፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስን ነውና፡፡» MYPAmh 149.6

ወደ ሥራው ለታይታ አገልግሎት የሚገቡ ሰዎች ሥራቸው የሰዎችን ወይንም የመላእክትን እይታ አያልፍም፡፡ ለስኬታማ ሥራ አስፈላጊ የሆነ ነገር ክርስቶስን ማወቅ ነው፡፡ ይህ እውቀት ስለ ትክክለኛ ነገር ጤናማ መርህን ይሰጣል፤ እንደዚሁም እናገለግለዋለን የምንለውን አዳኝ ባሕርይ የመሰለና የከበረ ራስ ወዳድነት የሌለው መንፈስ ይሰጣል፡፡ ሥራችን ሁሉ በወጥ ቤት ይሁን በሱቅ፣ በሕትመት ቢሮአችን ይሁን በጤና ተቋማችን፣ በኮሌጅ ይሁን ወይም በጌታ የወይን ቦታ፣ በተሰጠን በማንኛውም ሥፍራ በታማኝነት፣ በቁጣባ፣ በመጠንቀቅና በሙሉነት መገለጽ አለበት፡፡ «በጥቂት የታመነ በብዙም የታመነ ይሆናል፤ በጥቂት ያልታመነ በብዙም ያልታመነ ይሆናል፡፡» Review & Herald, Sept. 22, 1891. MYPAmh 150.1