Go to full page →

ታማኝነትን ማጉደል ተመዝግቧል MYPAmh 149

አንድ ሠራተኛ በቀጥታ በጌታው እይታ ውስጥ ባለመሆኑ ምክንያት የተሰጠውን ሰዓት በአግባቡ መጠቀምን ችላ እንዲል የሚመረው ነገር እጅግ አስጸያፊ የሆነ ራስ ወዳድነት ነው፡፡ ነገር ግን እንዳልታወቀና ታማኝ አለመሆናቸው እንዳልተመዘገበ ሆኖ ይሰማቸዋልን? ዓይኖቻቸው ቢከፈቱ ኖሮ የእግዚአብሔር ጠባቂ መልአክ እንደሚመለከታቸውና ግድ የለሽነታቸው በሙሉ በሰማይ መጽሐፍት ተመዝግቦ መኖሩን ያዩ ነበር፡፡ MYPAmh 149.3

ለእግዚአብሔር ሥራ ታማኝ ያልሆኑት መርህ የሌላቸው ናቸው፡፡ በውስጣቸው የሚያነሳሳው ዓላማ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ትክክለኛ የሆነውን ነገር ለመምረጥ የሚመራቸው አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ባሪያዎች ሁልጊዜ በቀጣሪያቸው እይታ ውስጥ እንዳሉ ሊሰማቸው ይገባል፡፡ የቤልሻጽርን ዓለማዊ ግብዣ የተመለከተው በተቋማችን ሁሉ ውስጥ ነው፤ በነጋዴ መቁጠሪያ ክፍል ውስጥም አለ፤ በግል ሱቃችን ውስጥም አለ፤ የዚያን ተሳዳቢ ንጉሥ አስፈሪ ፍርድ የጻፉት ደም የለሽ እጆች በእርግጠኝነት እየመዘገቡ ናቸው፡፡ የቤልሻጽር ኩነኔ በእሳት ቃላት ተጽፏል፡፡ እነርሱም «ተመዘንህ፣ ቀለህም ተገኘህ» የሚሉ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ግዴታዎች መወጣት ካልቻላችሁ የእናንተም ፍርድ ተመሳሳይ ይሆናል፡፡ MYPAmh 149.4