Go to full page →

መሻትን አለመግዛት አዋራጅ ነው MYPAmh 154

የአእምሮ ማስተዋል ያላቸው ወንዶችና ሴቶች በማንኛውም ዓይነት መሻትን ባለመግዛት ምክንያት የግብረገብ ኃይሎቻቸው እንዲደነዝዙ ሲያደርጉ በአብዛኞቹ ልምዶቻቸው ከአህዛብ የሚሻሉት በጣም በአነስተኛ ደረጃ ነው፡፡ ሰይጣን ሰዎችን የአካል፣ የአእምሮና የግብረገብ ጤንነትን ችላ እንዲሉ በማድረግ ከሚያድነው ብርሃን ወደ ባህልና ፋሽን ያለማቋረጥ እየሳባቸው ነው፡፡ ታላቁ ጠላት የምግብ ፍላጎትና ስሜት የበላይነትን ከያዙ የአካል ጤንነትና የአእምሮ ብርታት በራስ ደስታ መሰዊያ ላይ እንደሚሰው ያውቃል፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰው ወደ ፈጣን ጥፋት እንዲደርስ ያደርጋል፡፡ የሰለጠነ አእምሮ ልጓሙን በመያዝ እንስሳዊ ዝንባሌዎችን ከተቆጣጠረና በግብረገብ ኃይሎች ሥር ካደረገ ፈተናዎቹን በመጠቀም የማታለል ኃይሉ በጣም አነስተኛ መሆኑን ሰይጣን በደንብ ያውቃል…፡፡ MYPAmh 154.4

በክርስትና ዓለም ውስጥ ካሉት ሰዎች አብዛኞቹ ራሳቸውን ክርስቲያኖች ብለው የመጥራት መብት የላቸውም፡፡ ልምዶቻቸው፣ ከመጠን ያለፈ አኗኗራቸውና ለአካሎቻቸው ያላቸው አጠቃላይ አያያዝ የአካል ህግን የጣሰና ከመጽሐፍ ቅዱስ መስፈርት ተፃራሪ ነው፡፡ በሕይወት ጉዞአቸው ለአካል ሥቃይና ለአእምሮና ለግብረገብ መላሸቅ እየሰሩ ናቸው፡፡ MYPAmh 155.1