Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መሻትን አለመግዛት አዋራጅ ነው

    የአእምሮ ማስተዋል ያላቸው ወንዶችና ሴቶች በማንኛውም ዓይነት መሻትን ባለመግዛት ምክንያት የግብረገብ ኃይሎቻቸው እንዲደነዝዙ ሲያደርጉ በአብዛኞቹ ልምዶቻቸው ከአህዛብ የሚሻሉት በጣም በአነስተኛ ደረጃ ነው፡፡ ሰይጣን ሰዎችን የአካል፣ የአእምሮና የግብረገብ ጤንነትን ችላ እንዲሉ በማድረግ ከሚያድነው ብርሃን ወደ ባህልና ፋሽን ያለማቋረጥ እየሳባቸው ነው፡፡ ታላቁ ጠላት የምግብ ፍላጎትና ስሜት የበላይነትን ከያዙ የአካል ጤንነትና የአእምሮ ብርታት በራስ ደስታ መሰዊያ ላይ እንደሚሰው ያውቃል፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰው ወደ ፈጣን ጥፋት እንዲደርስ ያደርጋል፡፡ የሰለጠነ አእምሮ ልጓሙን በመያዝ እንስሳዊ ዝንባሌዎችን ከተቆጣጠረና በግብረገብ ኃይሎች ሥር ካደረገ ፈተናዎቹን በመጠቀም የማታለል ኃይሉ በጣም አነስተኛ መሆኑን ሰይጣን በደንብ ያውቃል…፡፡MYPAmh 154.4

    በክርስትና ዓለም ውስጥ ካሉት ሰዎች አብዛኞቹ ራሳቸውን ክርስቲያኖች ብለው የመጥራት መብት የላቸውም፡፡ ልምዶቻቸው፣ ከመጠን ያለፈ አኗኗራቸውና ለአካሎቻቸው ያላቸው አጠቃላይ አያያዝ የአካል ህግን የጣሰና ከመጽሐፍ ቅዱስ መስፈርት ተፃራሪ ነው፡፡ በሕይወት ጉዞአቸው ለአካል ሥቃይና ለአእምሮና ለግብረገብ መላሸቅ እየሰሩ ናቸው፡፡MYPAmh 155.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents