Go to full page →

ራስን ማሸነፍ ሥራችን ነው MYPAmh 155

አካላችን በቁጥጥራችን ሥር መሆን አለበት፡፡ የእኛነታችን ከፍ ያሉ ኃይሎች አካላችንን መግዛት (መቆጣጠር) አለባቸው፡፡ ስሜቶች ለአእምሮ ፈቃድ መገዛት አለባቸው፡፡ የአእምሮ ፈቃድ ራሱ ደግሞ በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር መሆን አለበት፡፡ የአእምሮ ንጉሣዊ ኃይል በእግዚአብሔር ጸጋ በመቀደስ ሕይወታችንን መቆጣጠር አለበት፡፡ MYPAmh 155.2

እግዚአብሔር እንድንፈጽም የሚጠብቅብን ነገሮች ወደ ህሊናችን መምጣት አለባቸው፡፡ ወንዶችና ሴቶች ራስን ለማሸነፍ ሥራ፣ ለንጽህና አስፈላጊነት፣ ከእያንዳንዱ አዋራጅ የምግብ ፍላጎትና ከሚያረክሱ ልምዶች ለመጠበቅ መንቃት አለባቸው፡፡ የአእምሮና የአካል ኃይሎቻቸው በሙሉ የእግዚአብሔር ሥጦታ እንደሆኑና ለአገልግሎቱ ሊጠበቁ በሚችሉበት የተሻለ ሁኔታ መያዝ እንዳለባቸው የሚገልጸው እውነታ በአእምሮአቸው መስረጽ አለበት፡፡ The Ministry of Healing, P.130. MYPAmh 155.3