Go to full page →

ሊደረሱ የሚገቡ ከፍታዎች MYPAmh 31

ውድ ወጣቶች ሆይ የህይወታችሁ ዓላማና ተግባር ምንድን ነው? በዓለም ላይ ስምና ሥልጣን የሚያስገኝላችሁን ትምህርት ለማግኘት ከፍተኛ ጉጉት አላችሁን? ለመግለጽ የፈራችሁት ግን በውስጣችሁ አንድ ቀን የምሁርነት ቁንጮ ላይ የመቆም ከፍተኛ ጉጉት አላችሁን? አንድ ቀን በህግ አውጪና ህግ አስፈፃሚ ምክር ቤቶች በመገኘት የአገርን ህግ አውጪዎች መሆን ትፈልጋላችሁን? እነዚህ ፍላጎቶች ምንም ስህተት የለባቸውም፡፡ ሁላችሁም ወዳሰባችሁበት መድረስ ትችላላችሁ፡፡ በትንንሽ ስኬቶች መርካት የለባችሁም፡፡ ከፍ አድርገህ አልም፡፡ ወዳለምከው ግብ ለመድረስ ምንም አትቆጥብ፡፡ MYPAmh 31.1