Go to full page →

ኃይማኖት የህይወት መሰረት MYPAmh 31

የእውነተኛ ታላቅነት ሁሉ መሰረቱ ፈርሃ እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ ወደ ህይወት ግንኙነታችሁ ሁሉ ለእውነት የማይናወጥ ታማኝነት ይዛችሁ መሄድ ያለባችሁ መርህ ነው፡፡ ኃይማኖታችሁን ወደ ት/ቤት ህይወታችሁ፣ ወደ መማሪያ ክፍላችሁና ወደ ሥራ ቦታችሁ ሁሉ ይዛችሁ ሂዱ፡፡ ለእናንተ አስፈላጊ ጥያቄ መሆን ያለበት እንዴት አድርጋችሁ ያልዛገ የክርስትና ባህሪያችሁን በጥንካሬውና በንጽህናው ሥጋዊ ፍላጎታችሁንና ጥያቄዎቻችሁን በሙሉ ለክርስቶስ ወንጌል መርህ በማስገዛት መጠበቅ የሚያስችል ትምህርት መምረጥና መተግበር እንደምትችሉ ነው፡፡ MYPAmh 31.2

እግዚአብሔር ሲፈጥራችሁ በህይወታችሁ ያለውን ዓላማ መልስ ለመሥጠት ራሳችሁን ከማህበረሰቡና ከህይወት ጋር ለማገናኘት መስጠት የምትችሉትን አሁኑኑ ለመገንባት ትፈልጋላችሁ፡፡ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት ምድራዊ ስኬትን ከመፈለግ አልተከለከላችሁም፡፡ ነገር ግን ኃይማኖታችሁን ከእናንተ ጋር ወደ ሄዳችሁበት ሁሉ ይዛችሁ መሄድ አለባችሁ፡፡ በማንኛውም የሥራ ዘርፍ ራሳችሁን ብቁ ብታደርጉ የህይወትን መርህ መስዋዕት ብታደርጉ መከናወን እንደማይቻል የሚገልጽ ሐሳብን በፍፁም አታስተናግዱ፡፡ MYPAmh 31.3