Go to full page →

መጽሐፍ ቅዱስ እንደ አሰተማሪ MYPAmh 173

ቅዱሳት መጽሐፍት በአስተማሪነታቸው ተወዳዳሪ የላቸውም:: ሰዎች በእጃቸው ካላቸው ታሪክ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ጥንታዊና ሁሉን የሚያጠቃልል ታሪክ ነው። ከዘላለማዊ የእውነት ምንጭ አዲስ ሆኖ ነው የመጣው። በዘመናት ሁሉ መለኮታዊ እጅ ንፅህናውን ጠብቆ አቆይቷል። ሰብዓዊ ምርምር ሊደርስበት በከንቱ እየጣረ ያለውን እጅግ ሩቅ የሆነውን ያለፈውን ነገር ያበራል። የምድርን መሰረት የጣለውንና ሰማያትን የዘረጋውን ኃይል ማየት የምንችለው በእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው። በሰዎች ትዕቢትና የተሳሳተ ግንዛቤ ያልተበከለ የሰብዓዊ ዘር ታሪክ የሚገኘው እዚህ ብቻ ነው። MYPAmh 173.1