Go to full page →

ከፍ ያሉ ሀላፊነቶች MYPAmh 31

በመንፈሳዊ መርሆች ሚዛናችሁን ጠብቃችሁ ወደፈለጋችሁት የእድገት ደረጃ መውጣት ትችላላችሁ፡፡ እግዚአብሔር ወደ አቀደላችሁ የከበረ ከፍታ ስትወጡ ማየት ያስደስተናል፡፡ የሱስ የተከበሩ ወጣቶችን ይወዳል፡፡ ባልዳበሩና ባልተስተካከሉ መክሊቶች ሲያድጉ ማየት አይወድም፡፡ ለታላላቅ ኃላፊነቶች ገጣሚ እንዲሆኑ የሰለጠኑና ለዚሁ ጉዳይ ህጋዊ በሆነ መንገድ እያንዳንዱን ነርቫቸውን ሥራ ላይ የሚያውሉ ጽኑ የህይወት መርህ ያላቸው ጠንካራ ሰዎች ይሆናሉ፡፡ MYPAmh 31.4

ነገር ግን በእግዚአብሔር የተሰጡህን ኃይሎች ለክፋትና ሌሎችን ለማጥፋት የመጠቀምን ታላቅ ወንጀል በፍፁም አትፈጽም፡፡ የሥነ ምግባር ውድመትንና ጥፋትን ለማምጣት የተሰጣቸውን ችሎታ የሚጠቀሙ ተሰጥዖ ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡ ነገር ግን ይህን ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎች በመከሩ የማይኮሩበትን ዘር እየዘሩ ናቸው፡፡ በህብረተሰቡ ውስጥ በረከትን በመዝራት ፋንታ ዋይታና በሽታን ለመዝራት ችሎታቸውን መጠቀም አስፈሪ ነገር ነው:: እንደዚሁም የተሰጠንን መክሊት በለስላሳ ወረቀት ጠቅልሎ በዓለም ውስጥ መደበቅም አስፈሪ ነገር ነው፡፡ ይህን ማድረግ ማለት የህይወትን አክሊል መጣል ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይፈልጋል፡፡ ለእያንዳንዱ ሰው ሊሸከመው የሚገባ ሃላፊነት አለ:: የህይወትን ታላቅ ተልዕኮ መፈፀም የምንችለው እነዚህ ሃላፊነቶች ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ሲያገኙና በታማኝነትና በማስተዋል ሲተገበሩ ነው፡፡ MYPAmh 31.5