Go to full page →

የሃይማኖት ተፅእኖ MYPAmh 32

ጠቢቡ ሰው እንዲህ ይላል:- «በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ::” ነገር ግን ኃይማኖት ሀዘንተኛና ጭፍግግ በማድረግ የስኬትን መንገድ ይዘጋል ብለህ ለአንድ አፍታ እንኳን አትገምት፡፡ የክርስቶስ ኃይማኖት አንድንም የአካል ክፍል ዋጋቢስ ወይም ደካማ አያደርግም፡፡ ማንኛውንም እውነተኛ ደስታ እንዳትደሰት አያደርግም፡፡ በሕይወት ውስጥ ያለህን ፍላጎት ለመቀነስ ወይም ለጓደኞችና ለህብረተሰቡ ፍላጎት ግድየለሽ እንድትሆን የታቀደ አይደለም፡፡ ሕይወትን በማቅ አይሸፍነውም፡፡ ጥልቅ ትንፋሽ በመሳብና በመቃተት አይገልጽም፡፡ በፍፁም እንደዚህ አይደለም፡፡ በዓለም ውስጥ ደስተኛ የሆኑ ሰዎች እግዚአብሔርን በሁሉም ነገር የመጀመሪያ፣ የመጨረሻና ከሁሉም የተሻለ የሚያደርጉ ናቸው፡፡ ፈገግታና የፀሐይ ብርሃን ከፊታቸው ገፅ በፍፁም አይጠፋም፡፡ ኃይማኖት ተቀባዩን ሸካራና ጉርብጥብጥ፣ ንጽህናና ትህትና የጎደለው አያደርግም፡፡ በተቃራኒው ግን ግለሰቡን ከፍ ከፍ ያደርገውና የከበራ ያደርገዋል፡፡ እንደዚሁም አመለካከቱን ይሞርዳል፤ ፍርድ አሰጣጡን ይቀድሳል፡፡ ለሰማያዊ መላእክት ማህበርተኝነትና ኢየሱስ ሊያዘጋጅ ለሄደው ቤትም ገጣሚ ያደርጋል፡፡ ኢየሱስ የደስታ ምንጭ መሆኑን በፍጹም አንርሣ፡፡ በሰዎች ሥቃይ አይደሰትም፡፡ ነገር ግን ደስተኞች ሆነው ማየት ይወዳል፡፡ MYPAmh 32.1

ክርስቲያኖች ብዙ የደስታ ምንጮች በቁጥጥራቸው ሥር አሉላቸው፡፡ ያለ አንደች ስህተት የትኞቹ ደስታዎች የተፈቀዱና ትክክል መሆናቸውን መናገር ይችላሉ፡፡ አእምሮን የማያጨልሙና ነፍስን ዝቅ የማያደርጉ መዝናኛዎችን በመዝናናት መደሰት ይችላሉ፡፡ እንደዚሁም ተስፋ የማያስቆርጥ፣ ለራስ ያለውን ክብር የማይቀንስና አሳዛኝ ተጽዕኖ የማይኖረውንና የደስታን መንገድ የማይዘጋውን መዝናኛ መደሰት ይችላሉ፡፡ ኢየሱስን ከእነርሱ ጋር ወደ ሄዱበት መውሰድ ከቻሉና በጸሎት የተሞላ ሕይወት ከኖሩ ሙሉ በሙሉ ከአደጋ የተጠበቁ ናቸው፡፡ MYPAmh 32.2