Go to full page →

ክፍል 9—ንባብና ሙዚቃ MYPAmh 177

ወጣት ወንዶችና ሴቶች እውነተኛ እውቀትን የሚሰጣችሁን ስነ-ጽሁፍ አንብቡ፣ እርሱም ለቤተሰብ በሞላ ድጋፍ ይሆናል። በአንክሮ •እንዲህ በሉ:- “ለራሴ ትርፍ የማላገኝበትንና ሌሎችን ለማገልገል ገጣሚ የማያደርገኝን ሥነ-ጽሁፍ በማንበብ ውድ ጊዜያቶቼን አላባክናቸውም። ጊዜዬንና ሐሳቦቼን ለእግዚአብሔር አገልግሎት ብቃትን ለማግኘት አውላለሁ። ከንቱና ኃጢአተኛ ለሆኑ ነገሮች ዓይኖቼን እጨፍናለሁ። ጆሮዎቼ የጌታ ስለሆኑ ጠላት የሚያቀርባቸውን የተንኮል ምክንያቶችን አልሰማም። ድምፄን በማንኛውም መንገድ በመንፈስ ቅዱስ ተፅዕኖ ሥር ከማድረግ ሌላ ለማንኛውም ፈቃድ ተገዥ አላደረገውም። አካሌ የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ስለሆነ የእኔነቴ እያንዳንዱ ኃይል ዋጋ ያላቸውን ነገሮች ለመሻት ይቀደሳል::” Testimonies for the Church, Vol 7, P. 64. MYPAmh 177.1