Go to full page →

የምናነበውን መምረጥ MYPAmh 178

ትምህርት ማለት የአካል፣ የአእምሮና የመንፈሳዊ ኃይሎችን የሕይወት ተግባራትን በተሻለ ሁኔታ ለመፈፀም ማዘጋጀት ነው። ነገሮችን የመቋቋም ኃይል፣ የአእምሮ ብርታትና ተግባር ጥቅም ላይ ባዋልናቸው ሁኔታ መጠን ሊቀንሱም ሊጨምሩም ይችላሉ። የአእምሮ ኃይሎች በትክክል እንዲያድጉ ከፈለግን አእምሮኣችን መገራት አለበት:: MYPAmh 178.1

ብዙ ወጣቶች መጽሐፍትን ለማንበብ ጉጉት አላቸው። ማግኘት የሚችሉትን ሁሉ ለማንበብ ይሻሉ። ስለሚያነቡትም ሆነ ስለሚሰሙት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። ተገቢ ባልሆነ ንባብ ምክንያት የመበላሸት ታላቅ አደጋ ውስጥ እንዳሉ መመሪያ ተሰጥቶኛል። ሰይጣን የወጣቶች አእምሮ እንዳይረጋጋ የሚያደረግበት ሺህ መንገዶች አሉት። ለአንዳፍታ እንኳን ከእግዚአብሔር ጥበቃ ውጭ መሆን አይችሉም። በጠላት ፈተናዎች እንዳይታለሉ በአእምሮዎቻቸው ውስጥ ጠባቂ ማስቀመጥ አለባቸው። MYPAmh 178.2