Go to full page →

ያልተሟላ ንባብ ተፅዕኖ MYPAmh 178

የአእምሮ ሁኔታ• በከፍተኛ ደረጃ በሚመገበው ነገር የሚወሰን መሆኑን ሰይጣን ያውቃል። ወጣቶችንም ሆነ በእድሜ የበሰሉትን የታሪክ መጽሐፍትን፣ አፈ-ታሪኮችንና ሌሎች የስነ-ጽሁፍ መጽሐፍትን እንዲያነቡ ሊመራቸው ይፈልጋል። የዚህ ዓይነት ስነ-ጽሁፍ አንባቢዎች ከፊታቸው ለሚጠብቃቸው ተግባር ገጣሚ አይሆኑም። የሚኖሩት ከእውነታ የራቀ ሕይወትን ስለሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ለመመርመርና ሰማያዊ መናን ለመመገብ ፍላጎት አይኖራቸውም። ብርታት የሚያስፈልገው አእምሮ ይደክምና ከክርስቶስ ተልእኮና ስራ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ታላላቅ እውነቶች ማለትም አእምሮን በማነፅና አስተሳሰብን በማንቃትና ልክ ክርስቶስ እንዳሸነፈ የማሸነፍን ጠንካራ ልባዊ ፍላጎት የማቀጣጠል ኃይል ያላቸውን እውነቶች የማጥናት •ኃይል ያጣል። MYPAmh 178.3