Go to full page →

ለመክሊቶቻችን መጋቢ መሆናችን MYPAmh 32

ወጣት ወዳጆቼ ሆይ! እግዚአብሔርን መፍራት የእድገት ሁሉ ዋና መሰረት ነው፡፡ የጥበብ መጀመሪያም ነው፡፡ የሰማዩ አባታችሁ ከናንተ የሚጠብቀው አለው፡፡ ሳትለምኑትና ምንም መልካም ነገር ሳይኖርባችሁ የልግስናውን በረከቶች ይሰጣችኋል፡፡ በዋጋ እንደተገዛችሁ ያውም በእግዚአብሔር ልጅ ውድ ደም የተሰጡአችሁን መልካም ዕድሎች በትክክል እንድትጠቀሙባቸው ይፈልግባችኋል፡፡ የአእምሮም ሆነ የግብረገብ ህይወታችሁ የእግዚአብሔር ሥጦታዎች ናቸው፡፡ በጥበብ እንድታሻሽሉአቸው የተሰጡአችሁን እነዚህን መክሊቶች በትክክል ባለመንከባከባችሁ ህይወት የለሽ አድርጋችሁ ልታስቀምጧቸው ወይንም ከተግባር የለሽነት የተነሳ ሽባና ድንክዬ እንድታደርጓቸው ነፃነት የላችሁም፡፡ እነዚያን ክብደት ያላቸውን ሃላፊነቶች በታማኝነት መፈፀም ወይም አለመፈፀም፣ ጥረቶቻችሁን በተሻለ ሁኔታና በትክክለኛ አቅጣጫ መምራት አለመምራት ውሳኔው የእናንተ ነው፡፡ MYPAmh 32.3

እየኖርን ያለነው በመጨረሻው ዘመን አደጋዎች ውስጥ ነው፡፡ እየመሠረታችሁ ባላችሁት ባህሪያት ላይ ሰማይ በሞላ ፍላጎት አለው፡፡ ከፍትወት በመነጨ በዓለም ውስጥ ካለው የሞራል ውድቀት አምልጣችሁ የመለኮታዊው ባህሪይ ተካፋዮች እንድትሆኑ እያንዳንዱ ሁኔታ ተመቻችቷል፡፡ ሰው በደካማ ጥረቱ የክፉ ኃይሎችን እንዲያሸንፍ ብቻውን አልተተወም፡፡ ለእያንዳንዷ እርዳታ ለምትሻ ነፍስ እርዳታው በቅርብ ነው፡፡ ያዕቆብ በራዕይ ባየው መሰላል ወደ ላይ ይወጡና ይወርዱ የነበሩ መላዕክት ከፍ ወዳለው ሰማይ እንኳን ለመውጣት ፈቃደኛ የሆነችውን ነፍስ ይረዳሉ፡ የእግዚአብሔርን ህዝብ እየጠበቁና እያንዳንዱን እርምጃቸውን እየተመለከቱ ናቸው፡፡ አንፀባራቂውን መንገድ የሚወጡ ይሸለማሉ፤ ወደጌታቸው ደስታም ይገባሉ፡፡» Fundamentals of Christian Education, PP. 82-86. MYPAmh 32.4