ከፍ ያለው ሰብዓዊ አስተሳሰብ መድረስ ከሚችለው በላይ ከፍ ብሎ ያለው እግዚአብሔር ለልጆቹ ያለው ግብ ነው፡፡ እግዚአብሔርን መምሰልና እውነተኛ መንፈሳዊነት ሊደረስበት የሚገባ ግብ ነው፡፡ በተማሪ ፊት ቀጣይነት ያለው የእድገት መንገድ ተከፍቷል፡፡ እያንዳንዱን መልካም፣ ንፁህና የከበረ ነገርን የሚያጠቃልል፣ ሊደረስበት የሚገባ ግብና መስፈርት አለ፡፡ በእያንዳንዱ እውነተኛ በሆነ የእውቀት ዘርፍ በተቻለው ፍጥነት መሄድ የሚችለውን ያህል ሁሉ ይገሰግሳል፡፡ ነገር ግን ጥረቶቹ ሰማይ ከምድር ከፍ ያለውን ያህል ከተራ ራስ ወዳድነትና ምድራዊ ፍላጎቶች ርቀው ከፍ ወዳሉ ግቦች መመራት አለባቸው፡፡ Education PP.18,19. MYPAmh 33.1