Go to full page →

መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ተወዳጅ መጽሐፍ MYPAmh 184

ሽማግሌዎችም ሆኑ ወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስን ችላ ይሉታል። መጽሐፍ ቅዱስን አያጠኑትም፣ የሕይወታቸው ህግም አያደርጉትም። በተለይ ወጣቶች በዚህ ቸልተኝነት በደለኞች ናቸው። አብዛኞቻቸው ሌሎች መጻሕፍትን ለማንበብ ጊዜ ይኖራቸዋል፣ ነገር ግን የዘላለም ሕይወትን መንገድ የሚያሳይ መጽሐፍ ቅዱስ በየቀኑ አይጠናም። መጽሐፍ ቅዱስ ችላ ተብሎ ዋጋ ቢስ የሆኑ መጻሕፍት በደንብ ይነበባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ከፍ ያለና ቅዱስ ሕይወት እንድንኖር የሚመራን መጽሐፍ ነው፡፡ወጣቶች ልበ-ወለድ ታሪኮችን በማንበብ አስተሳሰባቸው ባይዛባ ኖሮ መጽሐፍ ቅዱስን እስካሁን አንብበው ከሚያውቁኣቸው መጽሐፍት ሁሉ እጅግ ተወዳጅ ነው ይሉት ነበር። MYPAmh 184.1

የወጣትነት አእምሮዎች ከፍተኛ የጥበብ ምንጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ቸል ሲሉ እጅግ ከፍ ወዳለው የእድገት ደረጃ ሳይደርሱ ይቀራሉ። በእግዚአብሔር ዓለም ውስጥ በፈጣሪ ፊት መገኘታችን፣ በእርሱ አምሳያነት መሰራታችን፣ እንደሚመለከተን፣ እንደሚወደንና እንደሚጠነቀቅልን ማወቃችን አእምሮን ከፍ ወዳለው ማሰላሰል የሚመሩ አስደናቂ ጉዳዮች ናቸው። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ለማሰላሰል አእምሮውንና ልቡን የሚከፍት ሰው ተራ በሆኑ ስሜት አነሳሽ ነገሮች በፍጹም አይረካም። MYPAmh 184.2

ሁሉን አቀፍ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ •እውቀትን የመሻት ጠቃሚነቱን መገመት አይቻልም። “በእግዚአብሔር መንፈስ የተሰጠና •እኛን ለደህንነት ጠቢባን» ሊያደርገን የሚችል፣ የእግዚአብሔር ሰው “ለመልካም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀና ፍፁም” እንዲሆን ማድረግ የሚችል መጽሐፍ ቅዱስ በአክብሮት የተሞላ ትኩረታችንን በከፍተኛ ሁኔታ ይሻል። ጥልቀት በሌላው እውቀት የረካን መሆን የለብንም! ነገር ግን የእውነትን ቃላት ሙሉ ትርጉም ለመማርና ከተቀደሱ መጻሕፍት ጥልቅ መንፈስ ለመጠጣት መማር አለብን። Counsels Teachers, Parents and Students, p. 138-139. MYPAmh 184.3