Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

መልዕክት ለወጣቶች

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ ተወዳጅ መጽሐፍ

    ሽማግሌዎችም ሆኑ ወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስን ችላ ይሉታል። መጽሐፍ ቅዱስን አያጠኑትም፣ የሕይወታቸው ህግም አያደርጉትም። በተለይ ወጣቶች በዚህ ቸልተኝነት በደለኞች ናቸው። አብዛኞቻቸው ሌሎች መጻሕፍትን ለማንበብ ጊዜ ይኖራቸዋል፣ ነገር ግን የዘላለም ሕይወትን መንገድ የሚያሳይ መጽሐፍ ቅዱስ በየቀኑ አይጠናም። መጽሐፍ ቅዱስ ችላ ተብሎ ዋጋ ቢስ የሆኑ መጻሕፍት በደንብ ይነበባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ከፍ ያለና ቅዱስ ሕይወት እንድንኖር የሚመራን መጽሐፍ ነው፡፡ወጣቶች ልበ-ወለድ ታሪኮችን በማንበብ አስተሳሰባቸው ባይዛባ ኖሮ መጽሐፍ ቅዱስን እስካሁን አንብበው ከሚያውቁኣቸው መጽሐፍት ሁሉ እጅግ ተወዳጅ ነው ይሉት ነበር። MYPAmh 184.1

    የወጣትነት አእምሮዎች ከፍተኛ የጥበብ ምንጭ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ቸል ሲሉ እጅግ ከፍ ወዳለው የእድገት ደረጃ ሳይደርሱ ይቀራሉ። በእግዚአብሔር ዓለም ውስጥ በፈጣሪ ፊት መገኘታችን፣ በእርሱ አምሳያነት መሰራታችን፣ እንደሚመለከተን፣ እንደሚወደንና እንደሚጠነቀቅልን ማወቃችን አእምሮን ከፍ ወዳለው ማሰላሰል የሚመሩ አስደናቂ ጉዳዮች ናቸው። በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ለማሰላሰል አእምሮውንና ልቡን የሚከፍት ሰው ተራ በሆኑ ስሜት አነሳሽ ነገሮች በፍጹም አይረካም።MYPAmh 184.2

    ሁሉን አቀፍ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ •እውቀትን የመሻት ጠቃሚነቱን መገመት አይቻልም። “በእግዚአብሔር መንፈስ የተሰጠና •እኛን ለደህንነት ጠቢባን» ሊያደርገን የሚችል፣ የእግዚአብሔር ሰው “ለመልካም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀና ፍፁም” እንዲሆን ማድረግ የሚችል መጽሐፍ ቅዱስ በአክብሮት የተሞላ ትኩረታችንን በከፍተኛ ሁኔታ ይሻል። ጥልቀት በሌላው እውቀት የረካን መሆን የለብንም! ነገር ግን የእውነትን ቃላት ሙሉ ትርጉም ለመማርና ከተቀደሱ መጻሕፍት ጥልቅ መንፈስ ለመጠጣት መማር አለብን። Counsels Teachers, Parents and Students, p. 138-139.MYPAmh 184.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents