Go to full page →

በኃጢአት የመጀመሪያዎቹ እርምጃዎች MYPAmh 183

ክርስቲያን ግልጽ የሆነ ኃጢአት ከመፈፀሙ በፊት በልቡ ውስጥ ዓለም ሳያውቀው ረጅም የዝግጅት ሂደት ይካሄዳል። አእምሮ ከንጽህናና ከቅድስና በአንድ ጊዜ ወደ እርኩሰት፣ ወደ ክፋትና ወደ ወንጀል አይወርድም። በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች ወደ ጨካኝና ሰይጣናዊ ደረጃ ለማውረድ ጊዜ ይጠይቃል። በማየት እንለወጣለን። ንፁህ ያልሆኑ አስተሳሰቦችን በመለማመድ ሰው ከዚህ በፊት ይፀየፋቸው የነበሩ ኃጢአቶች የሚያስደስቱት እስኪሆኑ ድረስ አእምሮውን ያስተምራል:: Patriarchs and Prophets, P. 459. MYPAmh 183.7