Go to full page →

ገለባና ስንዴ MYPAmh 185

ውድ ወጣቶች ሆይ፣ ታሪኮችን የያዙ መጽሔቶችን ማንበብን ተዉ። እያንዳንዱን ልበ-ወለድ መጽሐፍ አስወግዱ …። በሰይጣን ወኪሎች የተፈጠሩ አስቂኝ ፎቶዎችን የያዙ መጽሔቶችንና ጽሑፎችን ከቤቶቻችን ስናስወግድ መልካም እናደርጋለን። ወጣቶች እነዚህን በመሰሉ ነገሮች አእምሮአቸውን መመረዝ የለባቸውም:: “ገለባ ለስንዴ ምኑ ነው?” የክርስቶስ ተከታይ ነኝ ባይ ሁሉ እውነተኛና ዘላለማዊ ጠቀሜታ ያለውን ነገር ብቻ ያንብብ። MYPAmh 185.3

ራሳችንን እጅግ ለተከበሩ ተግባራት ማዘጋጀት አለብን። ዓለም መዳን ያስፈልገዋል….። ሊሰራ ካለው ታላቅ ሥራ አንፃር ማንኛውም ሰው ለራሱ ጥቅምም ሆነ ለእግዚአብሔር ክብር የማይሆኑ ነገሮችን በማከናወን ውድ ጊዜንና እግዚአብሔር የሰጠውን መንገዶች እንዴት ማባከን ይችላል? The Youth’s Instructor, August 14, 1906. MYPAmh 185.4