Go to full page →

ክርስቲያናዊ ባህርይን መገንባት MYPAmh 186

በወጣቶቻችን ያልታዩ አብይ ጠቀሜታ ያላቸው መጻሕፍት አሉ።

እነዚህ መጻሕፍት ችላ የተባሉበት ምክንያት ለእነርሱ አንዳንድ ቀላል ጽሑፎች የሚስቡ ስላልሆኑ ነበር። ክርስቲያናዊ ባህርይን ለማጎልበት ብቁ የሆኑ መጽሐፍትን አጥብቀው እንዲይዙ ወጣቶችን መምከር አለብን። የእምነታችን እጅግ አስፈላጊ ነጥቦች በወጣቶች አእምሮ ውስጥ መታተም አለባቸው። የእነዚህ እውነቶች ጭላንጭል ነበራቸው፣ ነገር ግን የመጽሐፍቱን አስተምሮ እንዲወዱት የሚመራቸው ያህል ትውውቅ አልነበራቸውም። ወጣቶቻችን ማንበብ ያለባቸው ለአእምሮዎቸው ጤናማና የመቀደስ ተፅዕኖ ያላቸውን ነገሮች ነው። ይህ የሚያስፈልጋቸው እውነተኛው ኃይማኖት ምን እንደሆነ መለየት እንዲችሉ እንዲያደርጋቸው ነው። ቅድስናን ማምጣት የማይችሉ ብዙ ጥሩ ንባቦች አሉ። MYPAmh 186.1

ለወጣቶች መሥራት ያለብን ጊዜና አጋጣሚ አሁን ነው። አሁን ያለነው አሰቃቂ የጭንቀት ጊዜ ውስጥ እንደሆነና እውነተኛውን አምልኮ ለይተን ማወቅ እንደምንፈልግ ንገሩአቸው። ወጣቶቻችን በትክክለኛ ሁኔታ መረዳት፣ መደገፍና መደፋፈር ያስፈልጋቸዋል። ይህ መሆን ያለበት እነርሱ እንደሚፈልጉት ሳይሆን የተቀደሱ አእምሮዎች እንዲኖራቸው በሚረዳቸው መንገድ ነው። ከማንኛውም ነገር ይልቅ ጥሩና የሚቀድስ ኃይማኖት ያስፈልጋቸዋል። MYPAmh 186.2

ረጅም እድሜን ለመኖር ተስፋ አላደርግም። ሥራዬ ተገባዷል። ለወጣቶቻችን የስንብት ቃላቶቼ ለሰማያዊ ኃይሎች እጅግ ማራኪ የሆነ ሕይወትን እንዲኖሩና እነርሱ በሌሎች ላይ የሚያሳድሩት ተፅእኖም እጅግ የከበሩ የሚያደርጋቸው እንዲሆን እንደምፈልግ •እንድትነግሩአቸው ነው። MYPAmh 186.3