Go to full page →

የተመረጠ የንባብ አቅጣጫ ተፈቀደ MYPAmh 186

በምሽት ጊዜ ለወጣቶች ጥቅም የሌላቸውን መጽሐፍት እየመረጥኩ እያስወገድኩ ነበር። እውነተኛ ሕይወትን እንዲኖሩ የሚያደፋፍሩና መጽሐፍ ቅዱስን ገልጠው ወደ ማንበብ የሚያደፋፍሩ መጽሐፍትን ምረጡላቸው:: ይህ ከዚህ በፊት በፊቴ የቀረበልኝ ሲሆን በፊታችሁ ላደርግና ለራሳችሁ እንድታደርጉት ላደርግ አሰብኩ። ለወጣቶቻችን ዋጋ ቢስ ንባቦችን መስጠት የለብንም። ለአእምሮና ለነፍስ በረከት የሚሆኑ መጽሐፍት ይፈልጋሉ:: እነዚህ ነገሮች እጅግ በቀላል ታይተዋል። ስለዚህ ህዝባችን እኔ እየነገርኩ ካለሁት ነገር ጋር መተዋወቅ አለበት። MYPAmh 186.4

ለህዝባችን ከዚህ የበለጠ ምስክርነት የሚኖረኝ አይመስለኝም። ፅኑ አእምሮ ያላቸው ሰዎቻችን ሥራውን ከፍ ለማድረግና ለመገንባት የሚጠቅም ምን እንደሆነ ያውቃሉ። ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፍቅር በልባቸው ውስጥ በማድረግ የእግዚአብሔርን ነገሮች በማጥናት እየጠለቁ መሄድ አለባቸው:: ወጣቶቻችን ተገቢው የንባብ አይነት እንዲኖራቸው እጓጓለሁ። ያኔ አዛውንቶችም ይከተሉታል። ዓይኖቻችን በእውነት መንፈሳዊ ውበት ላይ ማተኮር አለባቸው። ጭንቅላታችንንና አእምሮአችንን ለእግዚአብሔር ቃል እውነቶች ክፍት ማድረግ አለብን:: ሰይጣን የሚመጣው ሰዎች ባልተጠነቀቁ ጊዜ ነው። የማስጠንቀቂያ መልእክቱ አንድ ጊዜ በመተላለፉ መርካት የለብንም:: በየጊዜው ደጋግመን መስጠት አለብን። MYPAmh 186.5

ንባብን ብዙ አእምሮዎችን እንዲስብና ተፅእኖ እንዲያሳድር እጅግ የሚስብ አድርገን መጀመር እንችላለን። ለተጨማሪ ሥራ ጊዜ ካለኝ ለወጣቶች የሚሆኑ መጻህፍትን ለማዘጋጀት በደስታ መርዳት አለብኝ። MYPAmh 186.6

የወጣቶች አእምሮ በሚቀድሰው የእግዚአብሔር እውነት እንዲነካና እንዲቀረፅ መሰራት ያለበት ሥራ አለ። ወጣቶቻችን ፍፅምና-በእምነትንና ለዘላለማዊ ሕይወት የሚያዘጋጀውን የባሕርይ ፍፅምና እውነተኛ ትርጉም እንዲያገኙ ልባዊ ምኞቴ ነው። ብዙ ዓመታት እኖራለሁ ብዬ አልጠብቅም! ስለዚህም ለወጣቶች ይህን መልዕክት እተውላቸዋለሁ! ያውም የሚሰሩት አላማ እንዳይጨናገፍ ነው። MYPAmh 187.1

ወጣቶች ሁልጊዜ የእግዚአብሔርን ክቡርነትና ፀጋ ከፍ ከፍ እንዲያደርጉ እንዲያደፋፍሯቸው ወንድሞቼን አደፋፍራለሁ። ስለ እውነተኛ ኃይማኖት ክቡርነት ስሜት ሁልጊዜ ስሩ፣ ፀልዩም። የእግዚአብሔርን ቅድስናና ፀጋ ብሩክነትና ማራኪነት አውጁ። ይህ ጉዳይ ቸል የተባለ በመሆኑ ሸክም ይሰማኛል። MYPAmh 187.2

ሕይወቴ ለረጅም ጊዜ እንደሚቆይ ማረጋገጫ የለኝም። ነገር ግን በጌታ ተቀባይነት እንዳገኘሁ ይሰማኛል። ክርስቲያኖች ተብለው የሚጠሩ ሰዎች ያላቸውን ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ስመለከት ምን ያህል እንደተሰቃየሁ እርሱ ያውቃል። እውነቱ በእኔ ህይወት መታየት ግዴታ እንደሆነና ምስክርነቴ ወደ ሰዎች መድረስ እንዳለበት ተሰምቶኛል። ጽሑፎቼ በውጭ አገሮች ባሉ ሰዎች እጆች እንዲገቡ ለማድረግ የምትችሉትን ሁሉ እንድታደርጉ እፈልጋለሁ። MYPAmh 187.3

ለወጣቶች ብዙ መንፈሳዊ ጥቅሞች እንዳሉአቸው ንገሩአቸው:: እውነት ወደ ሰዎች እንዲደርስ ልባዊ ጥረት እንዲያደርጉ እግዚአብሔር ይፈልግባቸዋል። እነዚህን ነገሮች እንድናገር የኔ ልዩ ኃላፊነት እንደሆነ ተሰምቶኛል። Fundamentals of Christian Education, P.547-549. MYPAmh 187.4