Go to full page →

የልበ-ወለድ ውጤት MYPAmh 188

ብዙ ወጣቶች “ትምህርቴን ለማጥናት ጊዜ የለኝም” ይላሉ። ነገር ግን ምን እያደረጉ ናቸው? አንዳንዶች እያንዳንዷን ደቂቃ ጥቂት ተጨማሪ ሳንቲሞችን ለማግኘት እያጨናነቁ ናቸው። ይህ በስራ የተጨናነቀ ሰዓት መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ እና የእርሱን ትምህርቶች ቢለማመዱበት ኖሮ ያለመጠን በመስራት ካተረፉት የበለጠ ትርፍ ያስገኝላቸው ነበር። በማያስፈልጉ ጌጣጌጦች የሚባክነውን ገንዘብ ያተርፍላቸው ነበር! እንደዚሁም የአእምሮን ብርታት በመጠበቅ እግዚአብሔርን የመምሰልን ምስጢር እንዲያስተውሉ ይረዳቸው ነበር። “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው::” MYPAmh 188.1

ነገር ግን እነዚህ ክርስቲያን ነን የሚሉ ወጣቶች የራሳቸውን ዝንባሌ በመከተል የልባቸውን ስጋዊ ፍላጎት ያሟላሉ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውድ እውነቶች ጋር እንዲተዋወቁ በእግዚአብሔር የተሰጣቸው የምህረት ጊዜ ልበ-ወለድና አፈ-ታሪኮችን ለማንበብ ተሰጥቷል። ይህ ልምድ አንዴ ከተመሠረተ ለማሸነፍ ከባድ ነው። ነገር ግን ለሰማያዊው ዓለም እጩ በሆኑ ሰዎች ሊደረግ ይችላል። መደረግም አለበት። MYPAmh 188.2

ታሪክን በማንበብ እንዲወሰድ የተፈቀደ አእምሮ ተበላሽቷል። አስተሳሰብ የታመመ ይሆናል፣ ግምታዊነት አእምሮን ይቆጣጠራል። ከዚህም የተነሳ ግልፅ ያልሆነ መረበሽና ያለ ማቋረጥ የአእምሮ ሚዛንን ለሚያዛባ ያልተሟላ የአእምሮ ምግብ እንግዳ የሆነ ፍላጎት ይፈጥራል። ዛሬ ልበ-ወለድ ጽሁፎችን በማንበብ አእምሮአቸው ሚዛን ያጣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአእምሮ በሽተኞች መጠለያ አሉ። ውጤቱ በአየር ላይ ቤተ መንግስት መገንባትና የፍቅር በሽተኝነት ስሜት ነው። Signs of the Times, February 10, 1881. MYPAmh 188.3